የዓለም የጤና ድርጅት በኣዲሱ ኮሮና ቫይረስ የሚወስደው የመከላከያ እርምጃዎች

ስለ ወረርሺኙ ኮቪድ 19 እነሆ የመጨረሻዎቹ መርጃዎች። ከዓለም ጤና ድርጅት ወደ ሃገሩ የጤና ባለስልጣንና የዞኑ ባለስልጣናት የሚተላለፉትን መረጃዎች በድረገጹ ይገኛል። በዚህ በሽታ ከሚጠቁ ሰዎች በብዛት በሽታው ቀለል ያለና ከብሽታው የሚድኑ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በጣም ኣደገኛ ነው። የራስህን ጤንነት ጠብቀህ ለሌሎችን ለመከላከል የሚቀጥሉትን እርምጃዎች ተከተል፦

ብዙውን ጊዜ እጅዎን
ከኣልኮል በተዘጋጀ መታጠብያ ወይም በውሃና በሳሙና እጆችህን ኣዘውትረህ በደምብ ኣጽዳ
ለምን? ከኣልኮል የተዘጋጀው ወይም በውሃና ሳሙና መታጠብ በእጅ ያለውን ቫይረስ ስለሚገድል

ከህብረተሰቡ ካለህ ግንኙነት፡ ካጠገበህ ካለው ሰው ያለንህ ርቀት ጠብቅ
ካጠገብህ ከሚያነጥሰውና ከሚያስለው ሰው፡ ብያንስ የ 1 ሜትር ርቀት ልዩነት ይኑርህ።
ለምን? ማንኛውም ሰው ሲያነጥሰው ወይም ስያስለው ከኣፉና ከኣፍንጫው ከሚረጨው ትናንሽ ፈሳሾች ቫይረሱ ሊኖር ስለሚችል። በሽታ ካለው ሰው በጣም ቅርርብ ካለህ ሲያስለው ቫይረሱ በቀላሉ ልያስተላልፍልህ ይችላል: የኮቪድ 19 ቫይረስ ጭምር።

አይንህ፣ ኣፍንጫህና ኣፍህ ኣትንካ
ለምን? እጃችን ብዙ ነገሮች ስለሚነካ በቀላሉ በቫይረሱም ሊበከል ይችላል። እጅህን ኣንዴ ከተበከለ፡ ለአይን ኣፍንጫና ኣፍ ያስተላልፋል፡ ቀጥሎ ቫይረሱ በሰውነጥ ውስጥ በመስረጽ እንድትታመም ያረገሃል።

የመተንፈሻ ንጽህናዎችን ለመጠበቅ ሃላፊነት ይኑርህ
ኣንተና ካንተ ዙርያ የሚገኙ ሰዎች የመትንፈሻ ንጽህናዎቻችሁን እንደምትጠብቁ ኣረጋግጥ። ይህም ማለት፡ ስያስላቹህና ስያስነጥሳቹህ ኣፋቹህና ኣፍንጫቹህ በክንዳቹህ ወይም በወረቀት ከተዘጋጀ መሃረብ መሸፈን። ወርቀቱ ኣንዴ ከተጠቀማቹሁበት ወድያው መጣል።
ለምን? የሚረጩትን ፈሳሾች ቫይረሱን ስለሚያስተላልፉ። የመተንፈሻ ንጽህና ዘዴህን በደንብ በመጠበቅ ህብረተሰቡን ከሳል፣ ከጉንፋና ከኮቪድ 19 ትጠብቃለህ።

በበሽታው እንደተጠቃህ ስሜት ካለህ ወይም ከተጠራጠርክ ከቤት ሳትወጣ፡ ለቤተሰብ ሓኪምህ፣ ለሕጻናት ሓኪም ወይም ለተረኛ ሓኪም ደውል፡ ወይ ክልሉ ባዘጋጀው ይእርዳታ ጥሪ ደውል።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ