በኮቪድ 19 የኣደጋ ግዜና የኣለም ኣቀፍ ጥበቃ እውቅና ኣሰጣጥ፡ ኣሰራር

የኮቪድ 19 ቫይረስ መስፋፋት በጣልያንና በኣለም ድንገተኛ ኣደጋ ነው

የሁላችንም ጤንነት ለማስጠበቅ ከምንኖርበት ቦታ ኣለመውጣት ነው። መውጣት ወይም መንቀሳቀስ ያለብን፡ ለስራ ኣስፈላጊነት፣ ለኣስፈላጊ ሁኔታዎች፣ በጤና ምክንያትና ወደ መኖርያችን ለመመለስ ብቻ መሆን ኣለበት።

ከነዚህ ውጪ ሲንቀሳቀስ የተገኘ፡ እንዲቀጣ ተወስነዋል።

የቫይረሱ መስፋፋት ለማስቆም፡ በኣለም ኣቀፉ ጥበቃ እውቅና ኣሰራር ላይ፡ በኣንዳንድ ገጽታዎች ተጽዕኖ የሚያሳድሩ እርምጃዎች ተወስደዋል።

3. ለኣለም ኣቀፍ ጥበቃ የጥገኝነት ጥያቄ ማመልከት ትፈልጋለህ?

የፖሊስ ደህንነት ጽ/ቤት (ኡፊቾ ኢሚግራ ስዮነ) ለህዝብ ዝግ ነው። የጥገኝነት ጥያቄ ፍላጎትህን ለማመልከት ግን ወደ ፖሊስ ጽ/ ቤት (ኴስቱራ) መሄድ ትችላለህ። ጥያቄህን በተቻለ ግዜ ይመዘገባል።

2. ከክልሉ ኮምሽን ለቃለ መጠይቅ ጥሪ ትጠብቃለህ ወይም የቃለ መጠይቁ ቀን በዚህ ቀናት ነበር?

የቫይረሱ መስፋፋት ለመከላለል፡ በዚህ ወቅት የክልል ጽ/ቤት ኮምሽኖች ዝግ ናቸው መጠየቅም ኣቋርጠዋል። ይህንን ድንገተኛ ኣደጋ እንደተጠናቀቀ በተመዘገብከው መሰረት ኮምሽኑ ለቃለ መጠይቅ ኣዲስ ቀጠሮ ይሰጠሃል።

ማስታወስ ያለብህ፡ ከኮምሽኑና ከመንግስት ጽ/ቤቶች የሚላኩልህ ማንኛውም መልእክቶች፡ ባሳወቅካቸው የመጨረሻ ኣድራሻህን ነው። ከፕሮጀክት ወይም ከመጠለያ ውጭ ከሆንክ፡ በምትኖርበት የቤት ደወል ስር ስምህን በደንብ እንደተጻፈ ኣረጋግጥ።

3. ለኣለም ኣቀፍ ጥበቃ ያቀረብከውን ጥያቄ፡ መልስ እየተጠባበቅክ ነው?

መልሱ በተዘጋጀ ግዜ፡ መልእክት ከነመልሱ ይደርሰሃል።

በነዚህ ቀናት ውስጥ ውጤቱን ከተቀበልክና የኣለም ኣቀፍ ጥበቃ ጥያቀህ እውቅና ካገኘህ፡ የድንገተኛ ኣደጋውን እንዳበቃ ወደ ፖሊስ (ኴስቱራ) በመሄድ የመኖርያ ፈቃድህን መጠየቅ ኣለብህ።

ውሳኔው ደርሶህ በውሳኔው ካልረካህና ይግባኝ ማለት ከፈለግክ፡ ማወቅ ያለብህ ኣሁን በድንገተኛ ኣደጋው በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የይግባኙ ቀን ገደብ ለግዜው ቆመዋል። ስለዚህ ይግባኙ ለማቅረብ ግዜ ኣለህ። ለማንኛውም በ ኢ-መይል ወይም በስልክ ከጠበቃህ ግንኙነት ማድረግ ትችላለህ። በ መጠለያ ወይም በፕሮጀክት ከሆንክ ደግሞ ከፕሮጀክቱ ህግ ኣማካሪ ግንኙነት ኣድርግ።

4. መርጃዎች ያስፈልጉሃል ወይም ወደ ኮምሽኑ የምትልካቸው ሰነዶች ኣሉ?

በዚህ ግዜ የኮምሽኑ ጽ/ቤት ለህዝብ ዝግ ናቸው፡ በማንኛውም ግዜ ግን ለሚመለከተው ኮምሽን ኢ- መይል መላክ ትችላለህ። ቀጥሎ የተያያዙት መገናኛዎች ተመልከት

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ