ትኩረት፦ ከውጭ ሃገር የሚመለሱ ጣልያንያውያን እና የውጭ ዜጎች በጣልያን

ለማውረድ እዚህ ይጫኑ:

1. በጣሊያን ውስጥ ለመንቀሳቀስ በራስ የሚዘጋጅ የመንቀሳቀሻ ሰነድ፡ ኣዲስ ሞዴል 26.03.2020 NUOVO MODELLO 26.03.2020

2. በራስ የሚዘጋጅ የመንቀሳቀሻ ሰርተፊኬት ወይም ሰነድ፡ ሞዴል MODELLO

 • ከ 12 ማርች ቦኃላ፡ ከውጭ ወደ ጣልያን ለመግባት የሚያገለግሉ ህጎች የትኞቹ ናቸው?
 1. የትራንስፖርቱ ማመላለሻም ሃላፊነት ይወስዳል፡ በራስ የሚሞላው የጉዞ ምክንያት ሰነድ (የሞዴሉ ሊንክ)፡ በመውጫ ሰዓት ሞልቶ የሚተወው የጉዞው ምክንያት በደንብ መግለጽ ኣለበት በ (ጤና፣ ስራ፣ ኣስፈላጊ ጉዳዮች)። ለ 14 ቀናት ተወሽቦ የሚቆዩበት ቦታም ማሳወቅ። መዳረሻው እንደደረሱ የሚጠቀሙት ማጓጓዣ ወይም የራስ ማጓጓዣ የሚጠቀሙ ከሆነ፡ የሚገኙበት ስልክ ቁጥር የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር ጭምር ማሳወቅ። የጉዞው ምክንያት ኣስፈላጊ በመሆኑ፡ በድረግጻችን ካሰፈርናቸው ምክንያቶች ይመልከቱ።link al modulo 
 2. ከውጭ የሚመጡ ሰዎች የህዝብ ማጓጓዣዎች መውሰድ አይችሉም፡ መውሰድ ያለባቸው በግል ማጓጓዣ ብቻ ሲሆን፡ በመዳረሻ መጥቶ የሚወስዳቸው ( በ ኤርፖርት፣ ፖርት፣ ባቡር ጣብያ፥ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት፡ መኪና በመከራየት፡ በታክሲ ወይም የሚከራይ መኪና ከነ ሹፈሩ) ብቻ መሆን ኣለበት።   
 3. በኣሁኑ ሰዓት ማነኛውን ወደ ጣልያን የሚገባ ሰው ኳራንቴና ማድረግ ኣለበት። በግል መኪናው የሚገባም ጭምር። በስራ ወደ ጣልያን የሚገባ ኳራንቴናው ለማድረግ 72 ሰዓታት መቆየት ይችላል፡ በጣም ኣስፈላጊ በሆነ ምክንያት ብቻ (ለተጨማሪ 14 ሰዓታትም ማራዘም ይችላል)። 
 4. ሁሉም ከውጭ የሚገቡ ሰዎች፡ በግል መኪናቸውም ቢሆን፡ እንደገቡ ኃላፊነት ያለውን የአካባቢውን የጤና ባለሥልጣን ማሳወቅ አለባቸው ፡፡ 
 5. የሚወሸብበት፡ በቤቱ ብቻ ሳይሆን ባለጉዳዩ በሚመርጠው ቦታ መሆን ይቻላል።
 6. ኣንድ ሰው ወደ ጣልያን እንደገባ የኳራንቴና ውሸባ ግዜ የምያሳልፍበትቦታ ከሌለው (የሚቀበለው ሰው ከሌለ፣ በሆቴል ክፍል ካጣ ወዘተ ... ) የውሸባ ግዜው የሚያሳልፍበት፡ በባለጉዳዩ ወጪ፡ የሲቪል ጥበቃ በሚመድብለት ቦታ ይሆናል።
 7. ድንበር ተሻጋሪ ኣጓጓዦች፣ የሕክምና ሰራተኞች፣ የሰውና የጭነት ኣመላላሾች ይህን ህግ ኣይመለከታቸውም።

 

የጤና ሚኒስትሩ ትዕዛዝ ከመሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስትሩ ጋር በመመካከር 

 • በውጭ ኣገር የሚኖር የጣልያን ዜጋ ነኝ፡ ወይም ነዋሪነቴ በጣልያን የሆነ የውጭ ዜጋ ነኝ፡ ወደ ጣልያን መግባት እችላለሁ?

አዎ ፣ መመለስ በጣም አጣዳፊ ከሆነ። ስለዚህ ፣ ለምሳሌ ፣ ጊዜያዊ በሆነ ሁኔታ ወደ ውጭ አገር የሄዱ የጣልያን ዜጎች ወይም የውጭ ዜጎች (ለቱሪዝም ፣ ለንግድ ወይም ለሌላ) ተመልሰው ለመግባት ይፈቀዳል። እንደዚሁም፡ የሚሰሩበት ወይም የሚማሩበት ውጭ ሀገር ለመልቀቅ የተገደዱት የጣሊያን ዜጎችም ወደ ጣሊያን እንዲመለሱ ተፈቅዶላቸዋል (ለምሳሌ፣ ከስራቸው የተሰናበቱ፣ ቤታቸውን ያጡ፣ ትምህርታቸው ሙሉ በሙሉ ያቋረጡ)፡፡

 • እኔ የውጭ አገር ሰው ነኝ እና በአሁኑ ጊዜ ጣሊያን ውስጥ ነኝ፣ ወደ አገሬ መመለስ እችላለሁ?

አዎን ፣ የመመለሱ ጉዳይ ኣጣዳፊ ከሆነ፡ ልክ እንደ ጣልያኖች ከውጭ የሚመለሱበት ሁኔታ (ብዙ ግዜ የሚጠየቁና መልሰቹን እይ)። ግዝያዊ የስራ ማቆምና በቀጣይ የስራ መቆራረጥ ለመንቀሳቀስ ምክን ያት ሊሆኑ ኣይችሉም። ድንበሩን ለመድረስ አስፈላጊ ለሆኑት ምክንያቶች በራስየሚሞው ማረጋገጫ በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ድርገጽ ላይ የታተመው ቅፅ መጠቀም ይቻላል ፡፡

የቫይረሱ ስርጭትን በሚመለከት: የሚጓዙበት ሀገር የሚከተለውን እርምጃዎችና ሕጎች፡ ከመነሳትዎ በፊት በደንብ ማወቅ ይመከራል ፡፡ በተጨማሪ በጣልያን ያለውን የኣገሩ ኤምባሲ መጠየቅን ይመከራል።

 • ከውጭ እየተመለስኩ ነው ፡፡ ከአውሮፕላን ማረፊያ ፣ ከባቡር ጣቢያ ወይም ከመድረሻ ወደብ አንድ ሰው እንዲቀበለኝ መጠየቅ እችላለሁ?

አዎን ፣ ነገር ግን የሚፈቀደው፡ ለኣንድ በመኖርያ ቤት ኣብሮ ለሚኖረው ሰው ብቻ፡ በተቻለ መጠን ለቫይረሱ ስርጭት መከላከያ ቁሳቁሶች በመጠቀም። ከውጭ የሚመለሰው ሰው የሚመለስበት ኣጣዳፊ ምክንያት በመግለጽ፡ በኣገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በተዘጋጀው ቅጽ፤ የጉዞውን ዝርዝር ማለት ከየት ተነስቶ የት እንደሚያርፍና የሚያርፍበትን ኣድራሻ በቅጹ በደንብ ማስፈር ኣለበት።

ይህ እንዳለ ሆኖ፡ ጣልያን እንደገባ፡ የጤንነት ክትትል ለሚያደርገው የጤና ባለስልጣን ማሳወቅና ገለልተኛ ሆኖ የመቆየት ግዴታ ያለበት ሲሆን፡ በማንኛውም ግዜ የኮቪድ 19 የበሽታ ምልክት ከታየው በፍጥነት ለጤና ባለስልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ ኣለበት።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ