ከቤተሰብህ ለመቀላቀል የምትጠብቅ ከዕድሜ በታች የምትገኝ ታዳጊ ነህ?

ሰላም!

“ደብሊ III” ባዘጋጀው የኣሰራር ደንብ ከቤተሰቦችህ ኣባል ጋር ለመገናኘት እየጠበቅክ ከሆነ፡ የሚከተሉትን መረጃዎች በጥንቃቄ ኣንብብ።

  • እንደምታውቀው ከ ኮቪድ - 19 የጤናው ድንገተኛ አደጋ ጊዜ ሁሉንም የአውሮፓ ህብረት አገሮችን ይመለከታል ፡፡ የሁሉም መንግስታት ዋና ዓላማ የሰዎችን ጤና መጠበቅ ነው። ይህ በአሁኑ ጊዜ የሚከናወነው በአገሮች ውስጥ እና በውጭ የሚገኙትን ጉዞ በመቀነስ ብቻ ነው ፡፡

  • በአሁኑ ሰዓት በኣሰራሩ ሂደት መጀመርያ ላይ ከሆንክ ኣንተና ኣውሮጳ ውስጥ ከሚገኘው በተሰብህ የሚመለከቱን ሰነዶች ለማፈላለግ ግዜውን ተጠቀምበት። ከተቻለ ፡ ፎቶግራፍ፣ የልደት የምስክር ሰርተፊኬት፣ መታወቅያ ወረቀት ወይም ዝምድናቹህን የሚያመለክት ማንኛውም ማስረጃ እንዲሊክልህ ቤተሰብህን ኣነጋግር።

  • ከድንገተኛ አደጋው ጋር የሚወሰዱት እርምጃዎች የመቀላቀልህ ሂደት ቢዘገዩም እንኳን የመሄድህን ጉዳይ አያግዱትም፡ እያጋጠመን ያለው ድንገተኛ ጊዜያዊ ነው: ለዘላለም አይቆይም፦ አትጨነቅ፣ ብቻ ታጋሽ መሆን ኣለብህ።

  • የቤተሰብ መልሶ መገናኘት ካመለከትክና 18 ዓመት ሊሞላህ ከሆነ፡ ወይም ካመለከት ቦኃላ ወድያው ከሞላህ ኣትጨነቅ። ምንም እንኳን 18 ዓመት ቢያልፍህም ያመለከትከውን ግን ሂደቱ ይቀጥላል።

  • ዕድሜህ 18 ዓመት ሊደርስ ከተቃረበና ከኣውሮጳ ህብረት ካለው ቤተሰብህ ለመቀላቀል ከፈለግክ፡ ግን በቤተሰብ መልሶ ማገናኛ ገና ካላመለከትክ፡ ወድያውኑ ያንተ ሃላፊነት ለወሰደው ፣ ለኦፕሬተርህ ፣ ለህግ አማካሪህ ፣ ለማህበራዊ ሰራተኛች ኣነጋግር። ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉና ሊረዱህ ይችላሉ።

  • ጥርጣሬ ካለህ ስለዚህ ጉዳይ ተናገር፦ ኦፕሬተሩ ፣ ያንተ ሃላፊነት ለወሰደው ፣ የሕግ አማካሪው ኣንተንና ቤተሰብህ የሚደግፉ እዚህ አሉ እንዲሁም ጠቃሚ መረጃ ሊሰጡህ ይችላል ፡፡

ኣስታውስ፡ የዱብሊን ሕግ ወደ ቤተሰቦችህ ለማድረስ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ህጋዊ መንገድ ነውና ተረጋጋ።

ስለ መልሶ ማገናኘት ጥያቄዎች ካለህ የ EFRIS ፕሮጀክት መልስ ሊሰጥህ ይችላል፡ ደውልልን ፣ ጻፍልን ወይም ኦፐሬተርህ በ ኢ-መይል ኣድራሻችን እንዲያግኘን ጠይቅ። ኢ-መይል ኣድራሻችን፦ progettoefris@cidas.coop ወይም በስልክ ቁጥራችን +39 3404277780; +39 3428735259 ደውል።

የበለጠ መረጃ ከፈለግክ የጁማ ማፕ ድርጣቢያ https://coronavirus.jumamap.com/it_it/ ተመልከት፡ ወይም ለኑሜሮ ቬርደ ኦፐሬተሮች በ 800905570/3511376355 ደውል ወይም ኢ-መይል numeroverderifugiati@arci.it ጻፍልን።

(Thanks to CIDAS)

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ