የኮቪድ-19 ኣዲስ ሕጎችና ገደቦች ፡ ከ 4 እስከ 18 ሜይ 2020

በኤፕሪል 26-2020 የወጣው ኣዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ውሳኔ፡ ከ 4 ሜይ እስከ 18 ሜይ 2020 በስራ ላይ የሚውለው ለድንገተኛው የኮሮና ቫይረስ የነበረው ሕግ በመቀየርና ኣዲሱን ኣጠቃቀም በተግባር የሚያውል ስራ ይጀምራል።


ኣሁንም የግድ በኣካል መራራቅ ኣለብን?

ጭምብሎችና ጓንቶች ወይም ሌሎች መከላከያ መሳርያዎችን በመጠቀምና ቢያንስ የኣንድ ሜትር የኣካላዊ ርቀት መጠበቅ ግዴታ ሆኖ ይቆያል። ህዝብ የሚጠቀምባቸው ዝግ ቦታዎች ጭምብሎች መጠቀም ግዴታ ነው፡ በህዝብ ማጓጓዣዎችም ጭምር።.


ጉዞ ይፈቀዳል?

በኣንድ ክልል ውስጥ መጓዝ ይፈቀዳል፦ ለስራ፣ ለጤንነትን ለኣስፈላጊ ጉዳዮች እንዲሁም ቤተሰብ ለመጠየቅም ጭምር፡ ግን የኣንድ ሜትር የሰዎች መርራቅ በማክበርና ጭምብሎችን በመጠቀም ሲሆን መሰባሰብ ግን ሕጉን ኣይፈቀድም። ከክልል ውጭ መንቀሳቀስ የሚፈቀደው፡ ለስራ፣ ለጤንነት፣ ለኣስቸኳይ ጉዳይ ምክንያቶች ብቻ ነው። ወደ ቤት ወይም ወደ መኖርያ ቦታ መመለስ ይቻላል።

ለበለጠ መረጃ፡ ለድንገተኛ ኣደጋ ኮቪድ-19 ለተዘጋጀው የክልሉ ኑሜሮ ቬርደ ማነጋገርን ይመከራል። እንዲሁም ለሌሎች ኣስፈላጊ ጉዳዮች ወደ ክልልዎ ሲመለሱ፣ ለኳራንቴና እና ራስዎን ለማግለል ጭምር።


ኣዲሶቹ በራስ የሚዘጋጁ ማረጋገጫዎች የትኞቹ ናቸው?

በራስ የሚዘጋጅ የመንቀሳቀሻ ሰነድ

ወደ ጣልያን ለመግባት በራስ የሚዘጋጅ የማረጋገጫ ሰነድ

 

ወደ ፓርክ መሄድ እችላለሁ?

የልጆች የመወጫቻ ስፍራዎች በመዝጋትና ቢያንስ የኣንድ ሜትር ርቀት በማክበር ወደ መናፈሻዎች፣ የኣትክልት ስፍራዎችና የህዝብ መዝናኛ ቪላዎች መሄድ ይቻላል። የደህንነቱ ደንቦች ለማስከበር ካልተቻለ፡ ከንቲባዎቹ ወደ መናፈሻዎች የመግባት ሁኔታን መገምገም ይችላሉ።


ስፖርትና የኣካል እንቅስቃሴዎችን ማከናወን እችላለሁኝ? ከዕድሜ በታች የሆነ ከኔ ጋር መሄድ ይችላል?

በተናጠል ማከናወን ይቻላል። ለኣካለ መጠን ላልደረሱ ልጆችና በራሳቸው ለመንቀሳቀስ ሙሉ ኣቅም ከሌላቸው ሰዎች ጋር በመሄድ ስፖርት ወይም የኣካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከናወን የሚቻል ሆኖ፡ ለስፖርት ቢያንስ የሁለት ሜትር ርቀት ለሌሎች እንቅስቃሴዎች ደግሞ የኣንድ ሜትር ርቀት በመጠበቅ።

የቀብር ስነስርዓቶችና ሃይማኖታዊ ስነስርዓቶችን ማከናወን ይፈቀዳሉ?

የሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶችን በተመለከተ ቤተሰቡና የቅርብ ዘመዶች ለሚከበረው የቀብር ስነ ስርዓት መካፈል ይችላሉ፡ በክፍት ቦታ የሚዘጋጅ ከሆነ የሚመረጥ ሆኖ ጭምብሎችን በመጠቀምና የሰዎችን መርራቅ በመጠበቅ እስከ 15 ሰዎች መካፈል ይችላሉ።


ወደ ምግብ ቤት ወይም ወደ ፈጣን ምግብ ኣዘጋጆች መሄድ እችላለሁ?

አዎ ፡ ግን የታዘዙ ምግቦች ለመውሰድ ብቻ ነው። ለዚህም ምግብ ቤቶች የታዘዙ ምግቦች ለማድረስ ወይም ኣዘው ለሚወስዱ ሰዎች ክፍት ነው፡ የሰዎች መርራቅ እንደተጠበቀ ሆኖ፡ በምግብ ቤቱ ውስጥ መብላት ኣይቻልም። 


ትኩሳት ካለብኝ ምን ማድረግ አለብኝ?

ከ 37.5 ዲግሪ በላይ ትኩሳት ያለውና በመተንፈሻ ኣካላት ሕመም የሚሰማው ሰው፡ መጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን እቤት ውስጥ መቆየትና ሓኪሙን የማሳወቅ ግዴታ ኣለበት።


በሓኪም የታዘዘ መድሓኒት በኢ-መይል ወይም በሞባይል ስልክ መልእክት መቀበል ይቻላል?

ኣዎ፡በ19ማርች 2020 በወጣው ትእዛዝ መሰረት በሓኪም የሚላከው የኤለክትሮኒክ ኮድ ቁጥር በመጠቀም፡ ወረቀቱን በኣካል ከሓኪሙ መሳብ ኣያስፈልግም። ፋርማሲስቱ ኣንዴ የኤሌክትሮኒኩ ኮድ ቁጥርና የሕክምና መታወቅያ ኮድ (ኮዲቸ ፊስካለ) ካገኘ ቦኃላ የሚፈለገውን መድሃኒት ይሰጣል።.

በብሔራዊው የመገደብ እርምጃዎች ምክንያት ለሴቶች የጸረ ጥቃት ኣገልግሎት የሚሰጡ ማእከላት እንቅስቃሴኣቸውን ኣቁመዋል?

ኣላቆሙም፥ በሁከት የተጠመዱና በቁጡ መንፈስ እየተከታተሉ ከሚያስቸግርዋቸው፡ ሴቶች ብቸኝነት ሊሰማቸው ኣይገባም። ለ 24 ሰዓታት ኣገልግሎት ከሚሰጠውን ማእከል በነጻ ቁጥር 1522 በመደወል እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪ በጥቃት ክስተቱ ሴቶቹን ወደ ማእከሉ ለመሄድ ኣስፈላጊ በሚሆንበት ግዜ፡ መንቀሳቀስ እንደሚፈቀድላቸው በ 11 ማርች የወጣው ህግ ይጠቅሳል።

በአሁኑ ጊዜ ከ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተዛመደ ጭንቀት ውስጥ ላሉ ሰዎች የስነልቦና ድጋፍ ለማድረግ ተነሳሽነት አለ

በጤናና በሲቪል ጥበቃ ሚኒስቴር የሚተገበሩ የስነ ልቦና እርዳታ፡ የኑሜሮ ቨርደ ነጻ መደወያ ቁጥር 800.833.833 ከኤፕሪል 27 ጀምሮ ስራ ላይ ውለዋል። ከጣልያን ውጭም በ 02.20228733 መደወል ይቻላል። ሁልግዜ ከ 08:00 – 24:00 ድረስ በየቀኑ ይሰራል። መስማት የሚሳናቸውም መጠቀም የሚችሉበት የኣሰራር ሂደት ኣላቸው።

የበለጠ ለመረዳት ጤና ሚኒስቴር ለኣዲሱ ኮሮና ቫይረስ የስነልቦና ድጋፍ የኑሜሮ ቨርደ ድረገጽ ተመልከቱ። Numero verde di supporto psicologico .

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ