ከሜይ 18 ጀምሮ ለመጓዝ በሚመለከት የወጡ አዳዲስ ህጎች

በአጠቃላይ ከግንቦት 18 ጀምሮ ባለህበት ክልል ውስጥ ያለ ገደብ መሄድ ትችላለህ፡፡ ሆኖም ባለሥልጣኖቹ የኮቪድ - 19 ስርጭትን ለመግታት ወደ አንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች መጓዝ ሊገድቡ ይችላሉ።.

ከአንድ ክልል ወደ ሌላው የሚደረግ ጉዞ አሁንም ውስን ነው ፡፡ በአጠቃላይ በምትኖርበት ክልል ውስጥ መቆየት አለብህ፡፡ ወደ ሌላ ክልል ለመዘዋወር ብቸኛና ትክክለኛ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦ በስራ ምክንያት ከነማስረጃው በማቅረብ፣ በኣስቸኳይ ጉዳይ ምክንያት፣ በጤና ምክንያት ወይም ወደ ቤት ፡ ወደ መኖርያ ሰፈር ለመመለስ ነው።

በአጠቃላይ ከጁን 3 - ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ያለገደብ ለመንቀሳቀስም ይቻላል ፡፡ ሆኖም ባለሥልጣኖቹ የኮቪድ - 19 ስርጭትን ለመገደብ ወደ አንዳንድ የጣልያን አካባቢዎች መጓዝ ሊገድቡ ይችላሉ።

ኣሁንም ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ወይም በክፍት ቦታዎች መሰባሰብ ክልክል ነው። ለማንኛውም ወደምትፈልግበት ቦታ ለመሄድ ምን ማድረግ እንዳለብህ ኣዳዲስ መረጃዎች ለማግኘት፡ ክልልህን እያዘመነ የሚያወጣውን መረጃ በድረገጹ ተመልከት።.

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ