ለኣደጋ ግዜ የመልሶማቋቋምያ ገቢ ውሳኔ (Rem)

የኣደጋ ግዜ መልሶ መቋቋም ገቢ፡ በኮቪድ - 19 ድንገተና ኣደጋ ምክንያት ለቤተሰብ የሚደረግ የገቢ ድጋፍ ልኬት ነው። ይህ የገቢ ድጋፍ ሁለት ኮታዎች ያሉት ሲሆን እያንዳንዳቸው ከ 400.00 እስከ 800.00 ዩሮ ነው። ለዚህ ኣስፈላጊ መስፈርቶች፡ በጣልያን ነዋሪ መሆን፣ የንብረትና የገቢ መመዘኛዎች መለክያ (ISEE) ከ 15000.00 በታች ሲሆን ነው። መልሶ ማቋቋሙ፡ ከኮቪድ - 19 ድንገተኛ ሁኔታ ቦኃላ በመንግስት ከሚሰጡት ሌሎች እውቅናዎች ጋር ግኑኝነት የለውም። በተጨማሪ በቀጥታ ወይም በሌላ መንገድ ጡሮታ ከሚያገኙ (ከተለመደው ለኣካል ጉዳተኞች ከሚሰጠው በስተቀር)፣ ተቀጥረው የሚሰሩ ጠቅላላ ገቢያቸው ከተወሰነ ግምት ከፍ ያለ ከሆነ፣ የዜግነት ድጎማ ለሚያገኙ የቤተሰብ ኣካላት ተኳሃኝ ኣይደለም።

የኣደጋ ግዜ ገቢ ወይ ድጎማ ማመልከቻዎች እስከ ሰኔ 2020 ድረስ መቅረብ ኣለባቸው።

ለተጨማሪ መረጃ የኢንፕስ ድረገጽ ይመልከቱ፣ ፓትሮናቶ ያነጋግሩ ወይም ወደ ኣርቺ የነጻ የስልክ ቁጥር ይደውሉ።.

 

የመልሶ ማቋቋም ውሳኔ፡ ለሰራተኞች ኣዲስ እውቅና 

የመልሶ ማቋቋሙ ውሳኔ፡ የኮቪድ - 19 ድንገተኛ ኣደጋን ተከትሎ፡ ለሰራተኞች የሚሰጠው ካሳ ኣሳድሶ ኣካትተዋል:

  • በማርች ወር የ 600.00 ዩሮ እውቅና ያገኙ ነጻ ባለሙያዎች፣ ቀጣይ የስራ ውል ያላቸው፣ በግላቸው የሚሰሩ በልዩ መዝገብ የተመዘገቡ፣ ወቅታዊ የቱሪዝም ሰራተኞች፡ ኣሁንም ለኣፕሪል ወር የ 600.00 ዩሮ እውቅና ያገናሉ ወይም ይቀበላሉ።
  • በግብርና የሚሰሩ ሰራተኞች ለማርች ወር የ 600.00 ይሮ እውቅና ያገኙ፡ ለኣፕሪል 2020 የ 500.00 ዩሮ እውቅና ያገኛሉ።.
  • ነጻ ባለሙያዎች በ 2020 የሁለት ወር ገቢያቸው፡ ከ 2019 የሁለት ወር ገቢው ቢያንስ ከ 33% ከቀነሰ፡ ለመይ ወር የ 1000.00 ዩሮ እውቅና ያገኛሉ። ቀጣይ የስራ ውል ያላቸውና (CO.CO.CO)፣ በተለየ መዝገብ የተመዘገቡ ሰራተኞች ለመይ ወር የ 1000.00 ዩሮ እውቅና ያገኛሉ።
  • በቱሪዝም ዘርፍ ከ 1 ጀንዋሪ 2019 እስከ 17 ማርች 2020 ይሰሩ የነበሩና ያለፍላጎታቸው ስራውን ያቋረጡ ሰራተኞች ለመይ 2020 የ 1000.00 ዩሮ እውቅና ያገኛሉ።.
  • በኮቪድ - 19 ወረርሽን የተነሳ ስራቸውን ያቋረጡ ወይም የቀነሱ የተለያዩ ቅጥር ሰራተኞችና በግላቸው የሚሰሩ ሰራተኞች፡ ለኣፕሪልና መይ ወራት የ 600.00 ዩሮ ክፍያ ያገናሉ። (ከነዚህም ከቱሪዝም የተለየ ግዝያዊ ስራ ለሚሰሩና ተለዋዋጭ ስራ ለሚሰሩ)
  • የቤት ውስጥ ሰራተኞች፡ ለኣፕሪልና ለመይ ወራት ለእያንዳንዱ ወር የ 500 ይሮ ክፍያ ያገኛሉ።ኣንድ ወይም ከኣንድ በላይ ኮንትራት ያላቸውና በሳምንት ለኣስር ሰኣታት የሚሰሩና ከኣሰሪያቸው ጋር የማይኖሩ ከሆነ።.

ኣስፈላጊ፡ ለማርች ወር የ 600.00 ይሮ ድጋፍ ያልጠየቀ ሁሉ ኣዋጁ በታተመበት በ 15 ቀናት ውስጥ ማመልከት ኣለበት። ካላመለከተ ወደ ፓትሮናቶ ጽሕፈት ቤት ይሂድ ወይም የኢንፕስ ድረገጽ ይመልከት።.

ሁሉም መታወቅያዎች ለገቢው ዕውቅና ኣይሰጡም። እውቅና የማግኘቱ ወይም የመገለሉ ወይም እውቅና ለማግኘት እንዴት እንደሚጠየቅ የበለተ መረጃ ለማግኘት፡ ለኣርቺ የነጻ ቁጥር ደውል፣ የኢንፕስ ድረገጽ ተመልከት ወይም ወደ ፓትሮናቶ ሂድ።.

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ ወይም የነጻ ክፍያ ቁጥር 800905570 ይደውሉ።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ