ሕገ ወጥ የስራ ስምሪቶች ሕጋዊ ማድረግ

ከ 1 ጁን 2020 እስከ 15 ጁላይ 2020 ድረስ ሕገ ወጥ የስራ ግንኙነት እንዳይቀጥል ለማበረታታት የመኖርያ ፈቃድ (ፐርሜሶ ዲ ሶጆርኖ) ባልተለመደ መልኩ መጠየቅ ይቻላል። ውሉ መጠየቅ የሚቻለው ለ፦

  • ሀ) እርሻ፣ እርባታ፤ ኣሳ ማጥመድና ተመሳሳይ ስራዎች
  • ለ) ለግለሰብ ድጋፍ ስራ
  • ሐ) የቤተሰብ ፍላጎት ለማሟላት፡ የቤት ስራ.

ማመልከቻ ማስገባት የሚችሉ፦

  1. ኣሰሪዎች በጣልያን ውስጥ የሚገኙትን የውጭ ዜጎች ለመቅጠር ማመልከት ወይም መደበኛ ያልሆነ የስራ ግንኙነት በመኖሩ ኣሁንም በሂደት ያለውን የስራ ስምሪቱ ሕጋዊ ለማድረግ ማመልከት። የውጭ ኣገር ዜጎቹ ፎቶግራፋቸውና ኣሻራቸው የተወሰደላቸው ወይም ከማርች 8 በፊት ጣልያን ውስጥ የነበሩና ከዚህ ቀን ቦኃላ ጣልያን ኣገር ለቀው ያልወጡ መሆን ኣለባቸው።
  2. የውጭ ኣገር ዜጎች ከ 31 ኦክቶቨር 2019 ጀምሮ የወደቀ መኖርያ ፈቃድ ካላቸው፣ ያልታደሰ ወይም ወደ ሌላ ዓይነት ፈቃድ ካልቀየሩ፡ በጣልያን ውስጥ ለ 6 ወር የሚያገለግል ግዝያዊ መኖርያ ፈቃድ መጠየቅ ይችላሉ። የሚያመለክቱት የውጭ ዜጎች እስከ 8 ማርች በጣልያን ግዛት የነበሩና ከላይ የተጠቀሱትን የስራ ዓይነት ስራዎች የሰሩ መሆን ኣለባቸው። የውጭ ዜጎቹ በሚያገኙት የስድስት ወር መኖርያ ፈቃድ፡ የስራ ቅጥር ውል ከተፈራረሙ ቦኃላ፡ መኖርያ ፈቃዱ ወደ ስራ መኖርያ ፈቃድ ይቀየርላቸዋል። (በግብርና፣ በዓሳ ማጥመድ፣ በእርባታ፣ በግል ድጋፍ ወይም በቤት ውስጥ ስራ) ውል ከተፈራረሙ።

የሚያመለክቱት የውጭ ዜጎች እስከ 8 ማርች በጣልያን ግዛት የነበሩና ከላይ የተጠቀሱትን የስራ ዓይነት ስራዎች የሰሩ መሆን ኣለባቸው።

የውጭ ዜጎቹ በሚያገኙት የስድስት ወር መኖርያ ፈቃድ፡ የስራ ቅጥር ውል ከተፈራረሙ ቦኃላ፡ መኖርያ ፈቃዱ ወደ ስራ መኖርያ ፈቃድ ይቀየርላቸዋል። (በግብርና፣ በዓሳ ማጥመድ፣ በእርባታ፣ በግል ድጋፍ ወይም በቤት ውስጥ ስራ) ውል ከተፈራረሙ።

ማመልከቻው ተቀባይነት የማይኖረው፦

  1. 1 ስፖርቴሎ ኡኒኮ
  2. 2 ኴስቱራ ወይም በፖሊስ ኢሚግረሽን ጽሕፈት ቤት፡ የመኖርያ ፈቃዱን ለማግኘት. 

የስራ ስምሪቱ ሂደት ለማስተካከል፡ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የ 500 ዩሮ ክፍያ ግብር ከኩንባኛዎቹ ይከፈላል። ጥያቄው ከውጭ ዜጎች ከሆነ ግን ክፍያው የ 160 ዩሮ ነው።

ማመልከቻው ተቀባይነት የማይኖረው፦

ባለፉት ኣምስት ኣመታት ሕገ ወጥ ስደትን በመርዳት ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ኣሰሪ፣ በሕገ ወጥ ድርጊቶችና በኣመንዝራነት የሚያሳትፉ፣ ለኣካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በመቅጠር፣ በሕገ ወጥ ጣልቃ ገብነትና ጉልበት በመበዝበዝ ወንጀለኞች ለሆኑ ኣሰሪዎች።

ኣሰሪው በስፖተሎ ኡኒኮ የስራ ውል ካልተፈራረመ ወይም የውጭ ዜጋውን ካልቀጠረ።

ከጣልያን እንዲወጡ የተወሰነላቸው ወይም ወደ ክልሉ እንዳይገቡ የተከለከሉ፣ ወንጀል ሰርተው ለተቀጡ፣ ኣደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ፣ ሕገ ወጥ የውጭ ዜጎች እንቅስቃሴ ወይም ሌሎች ተዛማጅ ወንጀሎች የፈጸሙ፣ የሰዎች ነጻነት በመገደብ ወደ ሴተኛ ኣዳሪነት የሚያሰማሩና ከዕድሜ በታች ለሆኑ ሕፃናት ከሕግ ውጭ የሚያሰሩ የውጭ ዜጎች፡ ፍርዳቸው ባያልቅም ተቀባይነት የላቸውም።

ማነናውም ጥፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት በስርዓቱ ላይ እንደ ስጋት የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች ተቀባይነት የላቸውም።

ይህ ድንጋጌ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ በኣሰሪውና በሰራተኛው ላይ ያሉ የወንጀልና የኣስተዳደራዊ ሂደቶች ይታገዳሉ፡ እነሱም፦

  1. የሰራተኛው የስራ ቅጥር ማመልከቻ ካቀረቡ
  2. በሕገወጥ ለገቡና ትክክለኛ የመኖርያ ፈቃድ ለሌላቸው

ማመልከቻ ገብቶ ኣሰራሩ በሂደት ላይ እያለ፡ የውጭ ዜጋው በከባድ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሊባረር ኣይችልም።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ ወይም የነጻ ክፍያ ቁጥር 800905570 ይደውሉ።

Your Website Title
Ero Straniero

Ero Straniero Facebook

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ