ለኤኮኖሚያዊ እንቅስቅሴዎች ድጎማ

የሪፓርት ኢታልያ ድንጋጌ፡ በንግድ፣ በግል ስራ፣ በግብር ለሚተዳደሩ ወይም እስከ 31 ማርች 2020 ያልተዘጋ የንግድ ፈቃድ ላላቸው፡ ተመላሽ የማይሆን የገንዘብ ድጎማ እንዲያገኙ እውቅና ሰጥተዋል። 

ይህ ድጎማ የሚሰጣቸው በኣፕሪል 2020 ያስመዘገቡት ደረሰኝ፡ በኣፕሪል 2019 ካስመዘገቡት ሁለት ሰወስተኛው የቀነሰ ሲሆን ነው። ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ባይኖራቸውም ከ 1 ጀንዋሪ 2019 እንቅስቃሴ ለጀመሩም ድጎማ ይፈቀድላቸዋል።

በማንኛውም ሁኔታ መጠኑ ከ 1000 ዩሮ በታች እንዳይሆን ተወስነዋል ፦

  1. 1. 20% - በኣፕሪል 2020 እና በኣፕሪል 2019 መካከል ያለውን የመጨረሻው የገቢ ግብር ልዩነት ከ 400.000 ዩሮ የማይበልጥ ከሆነ

  2. 2. 15% - በኣፕሪል 2020 እና በኣፕሪል 2019 መካከል ያለውን የመጨረሻው የገቢ ግብር ልዩነት ከ 400.000 ዩሮ የሚበልጥከሆነ

  3. 3. 10% - በኣፕሪል 2020 እና በኣፕሪል 2019 መካከል ያለውን የመጨረሻው የገቢ ግብር ልዩነት ከ 1 ሚልየን ዩሮ የሚበልጥ ከሆነና ከ 5 ሚልየን ዩሮ ያነሰ ከሆነ

ይህ ተመላሽ የማይሆነው ድጎማ ለማግኘት ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ማመልከቻውን በኤለክትሮኒ መንገድ ለገቢዎች ኤጀንሲ (ኣጀንስያ ዴለ ኤንትራተ) ያቀርባሉ። ይህን ለማቅረብ ኣስፈጽሚዎች እንዲያስፈጽሙላቸው ውክልና መስጠት ይችላሉ።.  

በጁማማፕ በተጠቀሱት የፓትሮናቶ፣ የሰራተኞች ማሕበር ወይም የሕግና የኣስተዳደር እርዳታ ወደሚሰጡ ጽሕፈት ቤቶች እንዲሄዱ እንመክርዎታለን። 

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ