ስራን በሃላፊነት ማከናወን

እስከ የኮቪድ 19 የድንገተኛ ጊዜ ማብቂያ ድረስ ፣ ቢያንስ አንድ ልጅ ከ 14 ዓመት በታች ላላቸው፡ የግል ሴክተር ሠራተኞች፡ ከሥራው የራሱ ባህሪዎች ጋር የሚጣጣም እስከሆነ ድረስ ባሉበት ሥራውን የማከናወን መብት አላቸው። ስራ ያቆሙ ወይም ሥራ በሚቋረጥበት ጊዜ የገቢ ድጋፍ መሳሪያዎችን የሚቀበል በቤተሰብ ውስጥ ሌላ ወላጅ ሊኖር አይገባም፡፡ በተጨማሪም፡ በቤተሰብ ውስጥ የማይሠራ ሌላ ወላጅ ካለ ፣ ይህን ዓይነት ሥራን መቀበል አይቻልም። ስራውን ለማከናወን የሚያስችሉ የኤለክትሮኒክ መሳርያዎች (ለምሳሌ ኮምፒተር) ከኣሰሪው ካልቀረቡ ሰራተኛው ባለው መሳርያ መጠቀም ይችላል።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ