ለሽርሽር ጉርሻ

በሪፓርቲ ኢታልያ የጸደቀው ሕግ ተከትሎ፡ በ 2020 ገቢ መመዘኛው (ISEE) ከ 40.000 ዩሮ የማይበልጥ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች በተያያዘ፡ በኣገር ውስጥ በሚገኙ የቱሪስቱ መዝናኛዎችና ኣልጋና ቁርስ የሚሰጡ የንግድ ኣግሪቱሪዝሞች (bed & breakfast) ለሚከፈሉ ክፍያዎች ድጎማ ይሰጣል።

ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የሚሰጥ ድጎማ፡ በኣንድ የቤተሰቡ ኣባል ብቻ የሚከናወን ሆኖ እስከ 500.00 ዩሮ ይደርሳል። ድጎማው የቤተሰቡ ኣባላት ሲቀንስ፡ ይቀንሳል። በዚህም ምክንያት፡ ሁለት ሰው የያዘ ቤተሰብ የ 300.00 ዩሮ ድጎማ ሲሰጠው፡ ብቻውን ለሆነ ደግሞ 150.00 ዩሮ ይሰጣል።


1) ወጪው በኣንድ መፍትሔ ብቻ መሆን ኣለበት፡ ማለት፦ በኣንድ ኣግሪቱሪዝም ወይም ቤድ ኤንድ ብሬክፋስት ኣገልግሎት ሰጪ መሆ ኣለበት;

2) የወጪው ጠቅላላ ሰነድ በኤሌክትሮኒክ ፋክቱር ወይም የንግድ ደረሰኝ ከተጠቃሚው ፊስካል ኾድ የተያያዘ መሆን ኣለበት;

3) የኣገልግሎቱ ክፍያ፡ ያለ የቱሪዝም ኤጀንሲያዎችና ያለ ኤሌክትሮኒክ ድረገጽ ኣገልግሎት ሰጪዎች መከናወን ኣለበት።

ድጎማው ጥቅም ላይ መዋል የሚችለው በቅናሽ መጠን ላይ ፹% ያህል የሚሆነው ብቻ ሲሆን ቀሪው ፳% ደግሞ በተቀባዩየግብር ተመላሽ የሚታወቅ ነው።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ