ለብስክሌት መግዣ ቅናሽ (ቫውቸር)

በክልል ዋና ከተሞች፣ በከተሞች፣ በክፍለ ከተሞችና ከ 50.000 በላይ የሕዝብ ብዛት ያላቸው ማዛገጃ ቤቶች፡ ከዕድሜ በላይ ለደረሱ ሰዎች፡ ለብስክሌቶች መግዣ የሚውል “ቡዎኖ ሞቢሊታ” በሚል ቫውቸር ከመግዣው ዋጋ የ 60% ቅናሽ ያገኛሉ፡ ለማንኛውም ዋጋው ከ 500.00 ዩሮ መብለጥ የለበትም። ከ 4 መይ 2020 ጀምሮ (ሕጉ ከጸደቀበት ከ 26 ኤፕሪል 2020) እስከ 31 ዲክሰምበር 2020 ለ፦

  • ለግል መንቀሳቀሻ ኣገልግሎት የሚውሉ፡ በእግር የሚሽከረከሩ ብስክሌቶች፣ እንድሁም በኤሌክትሪክ የሚረዱ ብስክሌቶች እንደ ሴግወይ፣ ሆቨርቦርድ፣ ሞኖ ፓቲነና ሞኖ ዊል፡ መግዣ።


ይህ ቫውቸር ለኣንድ ግዜ ብቻ የሚጠየቅ ሆኖ ከተጠቀሱት ለኣንዱ መግዣ ይውላል።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ