ለተጓዦች ድጋፍ

ለስራ ወይም ለትምህርት ምክንያቶች የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቶችንና አካባቢያዊ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶችን የሚሰጡ ኩባንያዎች ተጠቃሚዎች፡ የማጓጓዣ ሰነዱ የመታደስ ጥያቄን ማቅረብ ይችላሉ፡ ለዚህም የሚከተሉትን ማሟላት ያስፈልጋሉ ፦

a) ፌብርዋሪ 23 ቀን 2020 በ ቁጥር 6 እና 25 ባወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ድንጋጌዎች መሠረት: በሥራ ላይ በሚውለው የመንግሥት እርምጃዎች በተሸፈነው ጊዜ ውስጥ ትክክለኛ የባቡር ወይም የአከባቢ የሕዝብ መጓጓዣ ሰነድ (ኣቦናሜንቶ) የነበራቸው፡

b) በ 28 ዲክሰምበር 2000፣ ቁጥር 455: የሪፓብሊኩ ፕሬዝዳንት ባወጣው ድንጋጌ መሠረት፡ የጉዞው ሰነድ በተጠቀሱት የመንግስት እርምጃዎች ምክንያት ሙሉውን ወይም በከፊል ለመጠቀም ያልቻሉ፡ በራስ የሚዘጋጅ ማረጋገጫ በመጻፍና ኃላፊነት በመውሰድ፡ ማመልከቻ ማቅረብ ይችላሉ፡፡


የጉዞ ቲኬቶችን ተመላሽ ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው፡ ጉዞዉን ኣለማከናወኑ ማስረጃ በማቅረብ፡ ጥያቄውን ለማጓጓዣ ትራንስፖርቱ ኣስተዳደር ማቅረብ አለበት። ኣስተዳደሩ ጥያቄው ከደረሰበት በ 15 ቀናት ውስጥ ተመላሹን፦


ላልተጠቀመበት የመጓጓዣ ሰነድ፡ በኣንድ ኣመት ውስጥ ሊጠቀምበት የሚችል ባውቸር ያዘጋጅለታል።


ሊጠቀምበት ያልቻለበት የመጓጓዣ ሰነዱ የሚሸፍን ማራዘያ ሰነድ ይሰጠዋል። 


በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ