ስራ በማቆም ምክንያት ለሚከፈሉ ልዩ ፈቃድ

ኮቪድ - 19፡ ስራ በማቆም ምክንያት ለሚከፈላቸው ማራዘምና ተጨማሪ ግዜ መስጠት

በኮቭድ - 19: ከ 23 ፈብርዋሪ እስከ 31 ኦገስት 2020 ስራ በማቆም ይከፈላቸው የነበረ ተጨማሪ 5 ሳምንታት ልዩ የዕረፍት ግዜ ይሰጣቸዋል። ይህ ለነበረው 9 ሳምንታት ተጨማሪ ማራዘምያ የሚጠቀሙበት ነው። ተጨማሪ የ 4 ሳምንታት ግዜ ከ 1 ሰፕተምበር እስከ 31 ኦክቶቨር 2020 ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። በቱሪዝም፣ በንግድ፣ በትልልቅ ስብሰባዎች፣ በመዝናኛ ፓርኮች፣ የቀጥታ ትርኢትና በሲነማ ላሉት ሰራተኞች፡ እነዚህ 4 ሳምንታት ከሰፕተምበር 1 በፊት መጀመር ይችላሉ።

ከ 12 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ላሉዋቸው ወላጆች፡ ከዚህ ቀደም ከታቀዱት 15 ቀናት ተጭማሪ ከ 5 ማርች እስከ 31 ጁላይ 2020 ልዩ የዕረፍት ቀናቱ ወደ 30 ቀናት ይራዘማል። በግል ስራ ተቀጥረው ለሚሰሩ ለልዩ ዕረፍቱ 50% ይከፈላቸዋል። የሕፃናት መዋያ ካልጠየቁና ሌላው ወላጅ ስራ ኣጥ ካልሆነ፣ ሰራተኛ ያልሆነ ወይም የገቢ ድጋፍ መሳርያዎች ተቀባይ ካልሆነ ልዩ ዕረፍቱ መጠየቅ ይችላል።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ