መብት በመስመር - ኑሜሮ ቬርደ ለወጣው የስራ ውል ማስተካከያ (Regolarizzazione)

800 999 977

ኣርቺ፡ ስለ ወጣው የስራ ውል ማስተካከያ በኑሜሮ ቬርድ መልስ ይሰጣል፡፡

ለስራ ውሉ ማስተካከያ በሚመለከት ይህ የመብት መስመር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ 9.00 – 13.00 እና ከ 14.30 – 18.30 ድረስ ይመልሳል፡፡ ነፃ የመብት መስመር ቁጥር በአሁኑ ወቅት በግብርና ወይም በግል እንክብካቤ አገልግሎቶች ውስጥ ለሚሰሩ፡ ስለ ስራ ውሉ አዳዲስ የአሠራር ህጎች መረጃ ለሚጠይቁ መልስ ይሰጣል ፡፡

ኣርቺ - በክልል ኮሚቴዎች አማካይነት አስፈላጊ መስፈርቶችን ላሟሉ ሁሉም የውጭ ዜጎች የሕግ ማዕቀፍ የማግኘት ዕድልን ይከተላል ፣ ይቆጣጠራል ፡፡ የመብት መስመሩ በጁማማፕ አውታረመረብ አገልግሎቶች በመጠቀም ማንኛውንም ሪፖርት የተደረጉ ማጭበርበሮችንና አድሎአዊ አሰራሮችን ይከሳል።

አገልግሎቱ ከመስመር ስልክና ከሞባይል ስልኮች ነፃ ሲሆን የአርቺ አውታረ መረብ የቋንቋ ኣስተርጓሚዎችን ይጠቀማል።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ