በመላው ብሔራዊ ክልል ውስጥ ኢንፌክሽኑን እንዳይዛመት ለመቆጣጠር አስቸኳይ እርምጃዎች - እስከ ኖቨምበር (ህዳር) 13 ቀን 2020 ድረስ የሚሰራ

የጭምብሎች ኣስገዳጅ ኣጠቃቀም

ጭምብሎች መለበስ ያለባቸው፥

  • በሁሉም ክፍት ቦታዎች
  • ጭምብሉ በክፍትም ይሁን በዝግ ቦታዎች ግዴታ ነው፡ ከቤትዎ በስተቀር

ጭምብሉን መጠቀም ለሚከተሉትን ግዴታ አይደለም፥

  • ከስድስት ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች
  • ጭምብልን ከመጠቀም የማይስማማ በሽታ ላላቸው ሰዎች ወይም የአካል ጉዳተኞች
  • የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በሚከናወንበት
  • የሚከተሉትን ልዩነቶች መሰረት በማድረግ፡ ከሌሎቹ ሰዎች ቢያንስ አንድ ሜትር የደህንነት ርቀትን መጠበቅ ሁልጊዜ ግዴታ ነው ፡፡

✓ የማህበረሰብ ጭምብሎች እንዲሁ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ፤ ማለትም የሚጣሉ ጭምብሎች ወይም የሚታጠቡ ጭምብሎች ፣ እራስዎንም የሚያመርቱ ቢሆንም ፣ በቂ መከላከያ ለመስጠት የሚችል እስከሆኑ ድረስ ፡፡

ስፖርትና አካላዊ እንቅስቃሴ

✓ የአካል እንቅስቃሴን በሚመለከት (ለምሳሌ በፍጥነት መራመድ) ብያንስ የ1 ሜትር ርቀት በመጠበቅ ማካሄድ ይፈቀዳል።

✓ ቢያንስ 2 ሜትር ርቀትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ግላዊ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን (ለምሳሌ መሮጥ) ማከናወን ይፈቀዳል

✓ በግል የሚካሄዱ መሰረታዊ የስፖርት እንቅስቃሴዎችና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በጂሞች ፣ በመዋኛዎች ፣ በስፖርት ማዕከሎችና ክለቦች (የህዝብና የግል) ሕጎችን እስከተከበሩ ድረስ፡ ማህበራዊ ርቀቶችን በመጠበቅና መሰባሰብን በማስወገድና ማከናወን ይፈቀዳሉ ፡፡

✘ የአማተር ስፖርትና፡ ከአማተር ስፖርት ጋር የተያያዙ ሁሉም ስፖርቶች የሚፈቀዱት በግለሰብ መልክ ብቻ ነው። የአማተር ውድድሮች የተከለከሉ ናቸው።

✓ ለጣልያን ብሔራዊ ወይም ክልላዊ ጥቅም፡ በግልና ብቡድን የሚካሄዱ የስፖርት ዝግጅቶችና ውድድሮች የሚፈቀዱት፡ በጣልያን ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴ (CONI) እውቅና ሲሰጣቸው ብቻ ነው።

✓ የስፖርት ውድድሮች (ለምሳሌ በስታዲየም)፡ ከሚይዘው መጠን እስከ 15% የሚሆነውን ተመልካች መኖር ይፈቀዳል እናም በክፍት ቦታ በማንኛውም ሁኔታ ከ 1000 በላይ ተመልካቾችና በዝግ ከ 200 አይበልጡም ፡፡ የአንድ ሜትር ርቀት ማስጠበቅና በመግቢያው የትኩሳት መጠን መለካት አለበት።

ዝግጅቶች ፣ ትያትሮች ፣ ሲኒማ ቤቶች ፣ የጭፈራ ቦታዎች

✓ ሲኒማ ቤቶች ፣ ቲያትሮችና ኮንሰርቶች ቢያንስ 1 ሜትር የደህንነት ርቀቱ በማክበር የሚቻል ሲሆን ቢበዛ 1000 ተመልካቾች በክፍት ትርኢቶችና በዝግ ትርኢቶች 200 ተመልካቾች እንዲኖሩ ተደርጓል ፡፡.

✘ በዳንስ ቤቶች ሆነ በጭፈራ ቤቶች የሚከናወኑ ዝግጅቶች ተከልክለዋል።

✘ የማህበረሰብ በዓላትና ትርዒቶች የተከለከሉ ናቸው ፡፡ ብሔራዊ እና ዓለም አቀፍ የንግድ ትርኢቶች እንደተፈቀዱ ይቆያሉ።

✓ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች፡ የስታቲክሱ መርህ በመከተል ማሕበርዊ ርቀቶች በማክበርና የተደነገገውን ሕግ በመከተል መደረግ ይቻላል።

✓ የመዝናኛ ኣዳራሾች፣ የካርታና የቢንጎ መጫወቻ ኣዳራሽች ከ 8:00 እስከ 21:00 ድረስ እንድያስተናግዱ ይፈቀድላቸዋል።

የሲቪል ወይም ሃይማኖታዊ ዝግጅቶችና ስብሰባዎች

✓ አሁን ላይ ያሉ ፕሮቶኮሎችንና መመሪያዎችን በማክበር ከሲቪል ወይም ከሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች የሚመነጩ በዓላት ከ 30 ሰዎች በማይበልጡ ተሳታፊዎች ሊከበር ይችላል።

✓ በርቀት ከሚካሄዱት ስብሰባዎች በስተቀር ስብሰባዎችና ኮንግረሶች ታግደዋል ፡፡ በግል የሚካሄዱ ስብሰባዎችም እንዲሁ በርቀት እንዲካሄዱ በጥብቅ ይመከራል።

የግል ድግሶች - በቤት ውስጥ ወይም ከቤት ውጭ

✘ የግል ድግሶች ከቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ የተከለከሉ ናቸው። በቤትዎ ውስጥ አብረው የማይኖሩ ከ 6 የማይበልጡ ሰዎችን ለመቀበል በጥብቅ ይመከራል ፡፡

ምግብ ቤቶች ፣ ቡና ቤቶች ፣ መጠጥ ቤቶች ፣ የኬክና የአይስክሬም ሱቆች
  • በጠረጴዛ ቁጭ ብለው ለሚስተናገዱ፥ ፡ ከ 5:00 እስከ 24:00 ይፈቀዳል። በጠረጴዛው የሚስተናገዱ የሰዎች ብዛት ከ 6 መብለጥ የለበትም።
  • ቆመው ለሚጠቀሙ ደንበኞች ከ 5:00 እስከ 18:00 ሰዓት ይፈቀዳል።
  • ወቅታዊ ደንቦችን በማክበር በታዘዙት መሰረት ምግብ በየብብቱ ማድረስ ይፈቀድላቸዋል።
ትምህርት ቤቶች

✓ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፡ የትምህርት ስዓታት ኣሰጣጡ የመግቢያ ሰዓቱ ወደ 9:00 የመራዘም እድል ይኖራል።

✘ በትምህርት ቤት የሚዘጋጁ ጉዞዎች የተከለከሉ ናቸው።

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ