ኣዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፕሬዝዳንት አዋጅ (DPCM): በዞኖች ገደቦች

ከዚህ በታች ሦስቱ የጣሊያን ወሳኝ አካባቢዎች: በጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዳር 3 ድንጋጌ፡ ከኖቬምበር 6 እስከ ታህሳስ 3 ድረስ የተደነገጉ ዋና ዋና ገዳቢ እርምጃዎች፡፡

ቢጫ አከባቢ
Lazio, Molise, Provincia autonoma di Trento, Sardegna, Veneto.

የኦረንጅ አካባቢ
Basilicata, Emilia Romagna, Friuli Venezia Giulia, Liguria, Marche, Puglia, Sicilia, Umbria.

ቀይ ዞን
Abruzzo, Calabria, Campania, Lombardia, Piemonte, Provincia autonoma di Bolzano, Toscana, Valle d’Aosta.

ቢጫ አከባቢ

 • ለተረጋገጡ የሥራ ምክንያቶች ፣ ለኣስፈላጊ ጉዳዮችና በአጠቃላይ ጤናን የሚመለከት እስካልሆነ ድረስ፡ ከሌሊቱ 22:00 ሰዓት እስከ ጥዋት 5:00 ሰዓት መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። በጤንነት ፣ በሥራ ፣ በትምህርት ፣ በአስፈላጊ ሁኔታዎች ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ላለመንቀሳቀስ ይመከራል።
 • ከፋርማሲዎች ፣ ፓራ ፋርማሲዎች ፣ ጤና ጣቢያዎች ፣ ሱፐር ማርኬቶች ፣ በሲጋራ መሽጫና በውስጡ ከሚገኙ የመጽሄትና ጋዜጣ መሽጫ በስተቀር በበዓላትና ቅድመ በዓላት (ቅዳሜ እና እሁድ) የገበያ ማዕከሎች ይዘጋሉ።
 • ሙዚየሞችና ኤግዚቢሽኖች ይዘጋሉ
 • ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ወይም ላብራቶሪ ለመጠቀም ካልሆነ በስተቀር፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የርቀት ትምህርት የሚከታተሉ ሲሆን፤ መዋለ ሕጻናት ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና የመለስተኛ ትምህርት ቤቶች: ትምህርት ቤት በመሄድ ይማራሉ። ለአዳዲስ ተማሪዎችና በላቦራቶሪዎች ለሚደረጉ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ካልሆነ በስተቀር ዩኒቨርሲቲዎች ተዘግተዋል።
 • ከትምህርት ቤት ትራንስፖርት በስተቀር በሕዝብ ማመላለሻ ላይ እስከ 50% ይቀንሳሉ።
 • የመጫወቻ ማዕከል ፣ ውርርድ ፣ የቢንጎና የቁማር ማሽን እንቅስቃሴዎች፡ በቡና ቤቶችና በሲጋራ መሸጫም ጭምር ታግደዋል።
 • ቡና ቤቶችና ምግብ ቤቶች ከምሽቱ 18:00 ሰዓት ይዘጋሉ። ይዞ መሄድ እስከ 22:00 ሰዓት ድረስ ይፈቀዳል። ለቤት ለማድረስ ምንም ገደቦች የሉም።
 • መዋኛ ፣ ጂሞች ፣ ቲያትር ቤቶችና ሲኒማዎች ይዘጋሉ። የስፖርት ማእከሎች ክፍት ሆነው ይቆያሉ።

የኦረንጅ አካባቢ

 • ለተረጋገጡ የሥራ ምክንያቶች ፣ ኣስፈላጊ ጉዳዮችና በአጠቃላይ ጤናን የሚመለከት እስካልሆነ ድረስ፡ ከሌሊቱ 22:00 ሰዓት እስከ ጥዋት 5:00 ሰዓት መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
 • በጤንነት ፣ በሥራ ፣ በትምህርት ፣ በአስፈላጊ ሁኔታዎች ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ፡ ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልልና ከአንድ ማዘጋጃ ቤት ወደ ሌላኛው መንቀሳቀስ ፡ መግባትና መውጣት የተከለከለ ነው።
  በሚኖሩበት ማዘጋጃ ቤት ውስጥም ቢሆን፡ የቀኑ አላስፈላጊ እንቅስቃሴዎች እንዲያስወግዱ ይመከራል።
 • በሳምንቱ 7 ቀናት፡ መጠጥ ቤቶችና ምግብ ቤቶች ዝግ ናቸው። ይዞ መሄድ እስከ 22:00 ሰዓት ድረስ ይፈቀዳል። ለቤት የታዘዘ ለማድረስ ምንም ገደቦች የሉም።
 • ከፋርማሲዎች ፣ ፓራ ፋርማሲዎች ፣ የምግብ አቅርቦት መሸጫዎች፣ ከሲጋራ መሽጫና በውስጡ ከሚገኙ የመጽሄትና ጋዜጣ መሽጫ በስተቀር፡ በበዓላትና ቅድመ በዓላት፡ የገበያ ማዕከሎች ይዘጋሉ።
 • ሙዚየሞችና ኤግዚቢሽኖች ይዘጋሉ
 • ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ወይም ላብራቶሪ ለመጠቀም ካልሆነ በስተቀር፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የርቀት ትምህርት የሚከታተሉ ሲሆን፤ መዋለ ሕጻናት ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና የመለስተኛ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ቤት በመሄድ ይማራሉ።
  ለአዳዲስ ተማሪዎችና በላቦራቶሪዎች ለሚደረጉ አንዳንድ እንቅስቃሴዎች ካልሆነ በስተቀር ዩኒቨርሲቲዎች ተዘግተዋል።
 • ከትምህርት ቤት ትራንስፖርት በስተቀር በሕዝብ ማመላለሻ ላይ እስከ 50% ይቀንሳሉ።
 • የመጫወቻ ማዕከል ፣ ውርርድ ፣ የቢንጎና የቁማር ማሽን እንቅስቃሴዎች፡ በቡና ቤቶችና በሲጋራ መሸጫም ጭምር ታግደዋል።
 • መዋኛ ፣ ጂሞች ፣ ቲያትር ቤቶችና ሲኒማዎች ዝግ ናቸው።
  የስፖርት ማእከሎች ክፍት ሆነው ይቆያሉ።

ቀይ ዞን

 • በሥራ ፣ በኣስፈላጊና በጤና ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በሚኖሩበት ማዘጋጃ ቤት ውስጥም ቢሆን በማንኛውም ጊዜ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ፡፡ ከአንድ ክልል ወደ ሌላውና ከአንድ ማዘጋጃ ቤት ወደ ሌላ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።
 • በሳምንቱ 7 ቀናት፡ መጠጥ ቤቶችና ምግብ ቤቶች ዝግ ናቸው። ይዞ መሄድ እስከ 22:00 ሰዓት ድረስ ይፈቀዳል። ለቤት የታዘዘ ለማድረስ ምንም ገደቦች የሉም።
 • ሱፐር ማርኬቶች ፣ አስፈላጊ የምግብ አቅራቢ ሱቆችና ከአስፈላጊ ነገሮች በስተቀር ሱቆች ዝግ ናቸው።
 • ጋዜጣ የሚሸጥበት፣ የትምባሆ መሸጫ ፣ ፋርማሲዎችና ፓራርማሲዎች ፣ የልብስ ማጠቢያ ፣ የቁንጅና ሳሎንና (ፓሩክየሪ) ፀጉር አስተካካዮች ክፍት ሆነው ይቆያሉ።
 • የውበት ማዕከሎች ተዘግተዋል።
 • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፣ የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ (በስኮላ ሜድያ)፤ የሁለተኛና የሰወስተኛ ዓመት ተማሪዎች የርቀት ትምህርት ይከታተላሉ።
  መዋእለ ሕፃናት፣ ኣንደኛ ደረጃና የመጀመርያ ዓመት የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ክፍት ናቸው። ለተለዩ ጉዳዮች ካልሆነ በስተቀር ዩኒቨርስቲዎች ዝግ ናቸው።
 • በ CONI እና በ CIP ለብሔራዊ ጥቅም ዕውቅና ከተሰጣቸው በስተቀር፡ የስፖርት ውድድሮች ታግደዋል ። በስፖርት ማዕከላት ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎች ታግደዋል። በቤት አከባቢ አካላዊ እንቅስቃሴና የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በግል መልክ ወይም ለብቻ በክፍት ቦታ ማከናወን ይፈቀዳል።
 • ሙዚየሞችና ኤግዚቢሽኖች ተዘግተዋል፤ እንዲሁም ቲያትር ቤቶች ፣ ሲኒማ ቤቶች ፣ ጂሞች ፣ የመጫወቻ አዳራሾች ፤ ውርርድ ፣ ቢንጎ ፡ በቡና ቤቶችና በሲጋራ መሽጫም ጭምር።.
  የተማሪዎች ማመላለሻ ካልሆነ በስተቀር፡ የህዝብ ማመላለሻዎች እስከ 50% ድረስ ብቻ እንዲጭኑ ይፈቀዳል።

እንቅስቃሴዎች፣ ማወቅ ያሉባቸው 6 ነገሮች

ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

የጉዞው ምክንያት በማንኛውም መንገድ መገለጽ አለበት? ራስን የጉዞው ምክንያት በጽሁፍ ማዘጋጀት ኣስፈላጊ ነው? ከ 5:00 ሰዓት እስከ 22:00 ሰዓት ድረስ መግለጽ አያስፈልግም ፡፡ አዎ፡ ከምሽቱ 22:00 ሰዓት እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ የጉዞው ምክንያት ሕጉ ከሚፈቀዱት መካከል መሆኑን ሁል ጊዜ ማሳየት መቻል አለብዎት። ራሱን የማይችል ዘመድ ወይም ጓደኛ ለመርዳት መሄድ እችላለሁ? አዎ፡ እሱ አስፈላጊ ሁኔታ ነው ስለሆነም የጊዜ ገደቦች የለውም ፡፡ ለማንኛውም ከ22:00 ሰዓት እስከ 5:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ግን ምክንያቱ መግለጽ ያስፈልጋል። ተለያይቻለሁ / ተፋትቻለሁ ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆቼን ለማየት መሄድ እችላለሁ? አዎ፡ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን ከሌላ ወላጅ ጋር ወይም በማንኛውም ሁኔታ ከአሳዳጊ ወላጅ ጋር ለመድረስ ወይም ከእርስዎ ጋር ለመውሰድ የሚደረጉት ጉዞዎች እንዲሁ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ማዘጋጃ ቤቶች መካከልም ይፈቀዳል። ወደ ቤተክርስቲያን ወይም ወደ ሌሎች የአምልኮ ቦታዎች መጓዝ እንችላለን? አዎ፡ ከ 5:00 ሰዓት እስከ 22:00 ሰዓት ብቻ። በአንዱ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ የምኖርና በሌላ ውስጥ የምሰራ ከሆነ “መመላለስ” እችላለሁ? አዎ ከቤታቸው ፣ ከመኖሪያ ቤታቸው ወይም ከመኖሪያ አከባቢያቸው ውጭ ያሉት እንደገና መግባት ይችላሉ? አዎ

ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

የጉዞው ምክንያት በማንኛውም መንገድ መገለጽ አለበት? ራስን የጉዞው ምክንያት በጽሁፍ ማዘጋጀት ኣስፈላጊ ነው? በሚኖሩበት ማዛጋጃ ቤት ውስጥ ከ 5:00 ሰዓት እስከ 22:00 ሰዓት ድረስ መግለጽ አያስፈልግም ፡፡ ወደ ሌሎች ማዘጋጃ ቤቶች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ፣ እንዲሁም ከሌሊቱ 22:00 ሰዓት እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ በእራስዎ ማዘጋጃ ቤት ውስጥም ቢሆን ፣ የጉዞው ምክንያት ሕጉ ከሚፈቀዱት መካከል መሆኑን ሁል ጊዜ ማሳየት መቻል አለብዎት። ራስዎ በሚጽፉት ማረጋገጫ ወይም በፖሊስ የተዘጋጀውን ቅጽ ሞምላት ይቻላል። ራሱን የማይችል ዘመድ ወይም ጓደኛ ለመርዳት መሄድ እችላለሁ? አዎ፡ እሱ አስፈላጊ ሁኔታ ነው ስለሆነም የጊዜ ገደቦች የለውም ፡፡ ተለያይቻለሁ / ተፋትቻለሁ ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆቼን ለማየት መሄድ እችላለሁ? አዎ፡ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን ከሌላ ወላጅ ጋር ወይም በማንኛውም ሁኔታ ከአሳዳጊ ወላጅ ጋር ለመድረስ ወይም ከእርስዎ ጋር ለመውሰድ የሚደረጉት ጉዞዎች እንዲሁ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ማዘጋጃ ቤቶች መካከልም ይፈቀዳል። ወደ ቤተክርስቲያን ወይም ወደ ሌሎች የአምልኮ ቦታዎች መጓዝ እንችላለን? አዎ፡ ከ 5:00 ሰዓት እስከ 22:00 ሰዓት ብቻ። ግን ከሌሊቱ 22:00 ሰዓት እስከ 5:00 ሰዓት ድረስ ከቀይ ዞኑ ወይም አከባቢ ጋር የሚዛመድ የእንቅስቃሴ ስርዓት አለ፡፡ በአንዱ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ የምኖርና በሌላ ውስጥ የምሰራ ከሆነ “መመላለስ” እችላለሁ? በቤት ውስጥ መሥራት የማይቻል ከሆነ በእነዚህ ጉዳዮች የእንቅስቃሴው ምክንያት ለስራ መሆኑን የሚያመለክት ቅጽ ሞምላት ያስፈልጋል። ከቤታቸው ፣ ከመኖሪያ ቤታቸው ወይም ከመኖሪያ አከባቢያቸው ውጭ ያሉት እንደገና መግባት ይችላሉ? ለስራ ምክንያት ፣ ለኣስፈላጊ ጉዳዮች ፣ ጥናት ወይም የጤና ምክንያቶች ወይም ማዘጋጃ ቤትዎ ውስጥ የማይገኙ ተግባሮችን ለማከናወን ወይም ለመጠቀም (ለምሳሌ ፣ ወደ ፖስታ ቤት መሄድ ወይም ግብይት ፣ እንደዚህ ያሉ ቢሮዎች ወይም የሽያጭ ቦታዎች በእራስዎ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ ከሌሉ)

ተደጋጋሚ ጥያቄዎች

የጉዞው ምክንያት በማንኛውም መንገድ መገለጽ አለበት? ራስን የጉዞው ምክንያት በጽሁፍ ማዘጋጀት ኣስፈላጊ ነው?

አዎ፡ የጉዞው ምክንያት ሕጉ ከሚፈቀዱት መካከል መሆኑን ሁል ጊዜ ማሳየት መቻል አለብዎት፡ ራስዎ በሚጽፉት ማረጋገጫ ወይም በፖሊስ የተዘጋጀውን ቅጽ በሞምላት ሊሆን ይቻላል።

ራሱን የማይችል ዘመድ ወይም ጓደኛ ለመርዳት መሄድ እችላለሁ?
ኣዎ፡ ኣስፈላጊ ከሆነ።

ተለያይቻለሁ / ተፋትቻለሁ ፣ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆቼን ለማየት መሄድ እችላለሁ?
አዎ፡ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን ከሌላ ወላጅ ጋር ወይም በማንኛውም ሁኔታ ከአሳዳጊ ወላጅ ጋር ለመድረስ ወይም ከእርስዎ ጋር ለመውሰድ የሚደረጉት ጉዞዎች እንዲሁ በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ማዘጋጃ ቤቶች መካከልም ይፈቀዳል።

ወደ ቤተክርስቲያን ወይም ወደ ሌሎች የአምልኮ ቦታዎች መጓዝ እንችላለን?
ከቤቱ በጣም ቅርብ ወደሆነው የአምልኮ ቦታ መድረስ ይቻላል ፣ ይህ ማለት ይህ እንቅስቃሴ በተቻለ መጠን በቤትዎ አካባቢ መሆን ኣለበት። በእርግጥ ስብሰባዎች እንዲወገዱ ከተደረገና ከሌሎቹ መካከል ከአንድ ሜትር ያላነሰ ርቀት ከተረጋገጠ የአምልኮ ቦታዎችን መሄድ ይፈቀዳል፡፡ የኣምልኮት ቦታዎች መሄድ የሚፈቀደው ሕጉን በተከተለ መሰረት መሆን ኣለበት፡ ማለትም ለስራ ምክንያት ኣስቀድሞ እንደተፈቀደው፡ በሃይማኖታዊ አገልግሎቶች ውስጥ ለመሳተፍም ይፈቀዳል ፡፡

በአንዱ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ የምኖርና በሌላ ውስጥ የምሰራ ከሆነ “መመላለስ” እችላለሁ?
በቤት ውስጥ መሥራት የማይቻል ከሆነ በእነዚህ ጉዳዮች የእንቅስቃሴው ምክንያት ለስራ መሆኑን የሚያመለክት ቅጽ ሞምላት ያስፈልጋል።

ከቤታቸው ፣ ከመኖሪያ ቤታቸው ወይም ከመኖሪያ አከባቢያቸው ውጭ ያሉት እንደገና መግባት ይችላሉ?
ለስራ ምክንያት ፣ ለኣስፈላጊ ጉዳዮች ፣ ጥናት ወይም የጤና ምክንያቶች ወይም ማዘጋጃ ቤትዎ ውስጥ የማይገኙ ተግባሮችን ለማከናወን ወይም ለመጠቀም (ለምሳሌ ፣ ወደ ፖስታ ቤት መሄድ ወይም ግብይት ፣ እንደዚህ ያሉ ቢሮዎች ወይም የሽያጭ ቦታዎች በእራስዎ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ ከሌሉ)

Fonte: http://www.governo.it/it/articolo/domande-frequenti-sulle-misure-adottate-dal-governo/15638

You may also like...

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ