ማህበራዊ እርዳታ

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) የድንገተኛ ግዜ ምክንያት መዘጋት ወይም ማቆም የሚያስከትለው ጉዳት ለመቋቋም፡ የጣልያን መንግስት፡ የኤኮኖሚ ኣቅም ለሌላቸው ፣ ሥራ አጥ ለሆኑና ቤተሰቦቹ ተከታታይ ማህበራዊ እርዳታዎችን ተግባራዊ አድርጓል ፡፡ በዚህ ገጽ፡ መንግስት ለሚያደገው ማሕበራዊ እርዳታዎችን በየግዜው በማደስ ያቀርባል።

ለቤት ሰራተኞችና ሽማግሌዎች ለሚንከባከቡ ቦኑስ ወይም ቫውቸር

ለቤት ሰራተኞችና ሽማግሌዎች ለሚንከባከቡ የሚሰጥ ቫውቸር ለኤፕሪልና ለመይ ወራት የ 500.00 ዩሮ በኢንፕስ በኩል ይከፈላል።

የሚከተሉትን በማሟላት ማመልከት ይቻላል፦

  • - በፌብርዋሪ 23 በሳምንት ከ 10 ሰዓታት በላይ የሚቆይ የቅጥር ኮንትራት ከነበረህ
  • - የስራ ሰዓትህ ከ25% ከቀነሰ
  • - ከዜግነት ገቢ በስተቀር ሌላ የምታገኘው ገቢ 600.00 ዩሮ የማይደርስ ከሆነ

 

ማመልከቻው በቀጥታ ለኢንፕስ ወይም በፓትሮናቶ በኩል መደረግ አለበት።INPS

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Bonus colf e badanti

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Bonus colf e badanti

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Bonus colf e badanti
JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Bonus colf e badanti

ከቤት ኣስገዶ ማስወጣትን ማገጃ

ህዝቡን ለመደገፍ መንግስት ባወጣው ሕግ ምክንያት ( የ 2020 ሕግ ቁጥር 27) ሁሉም አስገድዶ የማስወጣትና የቤት መልቀቅ ሂደቶች እስከ ሰፕተምበር 1 ቀን ድረስ ይታገዳሉ ፡፡

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Blocco degli sfratti

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Blocco degli sfratti

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Blocco degli sfratti

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Blocco degli sfratti

ኮቪድ - 19 ፡ ለሕፃናት መዋያና ለበጋ ማእከላት ተጨማሪ ቫውቸር

COVID-19: AUMENTO DEL BONUS BABY-SITTING e CENTRI ESTIVI

ለሕፃናት መዋያ ክፍያ የሚሰጠው ቫውቸር (ከበፊቱ 600.00 ዩሮ) ወደ 1200.00 ዩሮ ከፍ ይላል።ልኬቱ እስከ 16 ዓመት ዕድሜ ላላቸው ሕፃናት ወላጆች በግል ሴክተር ውስጥ የሚሰሩ ወይም የመንግሥት ሠራተኞች የሆኑ ግን በጤና ፣ በደህንነት ፣ በመከላከያ እና በህዝብ ማዳን ክፍል ውስጥ የሚሰሩ ከሆነ ብቻ ነው ፡፡ በተጨማሪም ቫውቸሩ ልጆችን በበጋ ማእከላት (centri estivi) ለልጆች ተጨማሪ አገልግሎቶችና በመሰረታዊ፡ማህበራዊ ትምህርት አገልግሎት በማስመዝገብ ላይ ሊውል ይችላል።

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Baby Sitting e centri estivi

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Baby Sitting e centri estivi

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Baby Sitting e centri estivi

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Baby Sitting e centri estivi

ለተጓዦች ድጋፍ

ለስራ ወይም ለትምህርት ምክንያቶች የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቶችንና አካባቢያዊ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶችን የሚሰጡ ኩባንያዎች ተጠቃሚዎች፡ የማጓጓዣ ሰነዱ የመታደስ ጥያቄን ማቅረብ ይችላሉ፡ ለዚህም የሚከተሉትን ማሟላት ያስፈልጋሉ ፦

a) ፌብርዋሪ 23 ቀን 2020 በ ቁጥር 6 እና 25 ባወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ድንጋጌዎች መሠረት: በሥራ ላይ በሚውለው የመንግሥት እርምጃዎች በተሸፈነው ጊዜ ውስጥ ትክክለኛ የባቡር ወይም የአከባቢ የሕዝብ መጓጓዣ ሰነድ (ኣቦናሜንቶ) የነበራቸው፡

b) በ 28 ዲክሰምበር 2000፣ ቁጥር 455: የሪፓብሊኩ ፕሬዝዳንት ባወጣው ድንጋጌ መሠረት፡ የጉዞው ሰነድ በተጠቀሱት የመንግስት እርምጃዎች ምክንያት ሙሉውን ወይም በከፊል ለመጠቀም ያልቻሉ፡ በራስ የሚዘጋጅ ማረጋገጫ በመጻፍና ኃላፊነት በመውሰድ፡ ማመልከቻ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

የጉዞ ቲኬቶችን ተመላሽ ማድረግ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው፡ ጉዞዉን ኣለማከናወኑ ማስረጃ በማቅረብ፡ ጥያቄውን ለማጓጓዣ ትራንስፖርቱ ኣስተዳደር ማቅረብ አለበት። ኣስተዳደሩ ጥያቄው ከደረሰበት በ 15 ቀናት ውስጥ ተመላሹን፦

ላልተጠቀመበት የመጓጓዣ ሰነድ፡ በኣንድ ኣመት ውስጥ ሊጠቀምበት የሚችል ባውቸር ያዘጋጅለታል።

ሊጠቀምበት ያልቻለበት የመጓጓዣ ሰነዱ የሚሸፍን ማራዘያ ሰነድ ይሰጠዋል። 

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ።

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Supporto Pendolari

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Supporto Pendolari

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Supporto Pendolari

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Supporto Pendolari

ለብስክሌት መግዣ ቅናሽ (ቫውቸር)

በክልል ዋና ከተሞች፣ በከተሞች፣ በክፍለ ከተሞችና ከ 50.000 በላይ የሕዝብ ብዛት ያላቸው ማዛገጃ ቤቶች፡ ከዕድሜ በላይ ለደረሱ ሰዎች፡ ለብስክሌቶች መግዣ የሚውል “ቡዎኖ ሞቢሊታ” በሚል ቫውቸር ከመግዣው ዋጋ የ 60% ቅናሽ ያገኛሉ፡ ለማንኛውም ዋጋው ከ 500.00 ዩሮ መብለጥ የለበትም። ከ 4 መይ 2020 ጀምሮ (ሕጉ ከጸደቀበት ከ 26 ኤፕሪል 2020) እስከ 31 ዲክሰምበር 2020 ለ፦

  • ለግል መንቀሳቀሻ ኣገልግሎት የሚውሉ፡ በእግር የሚሽከረከሩ ብስክሌቶች፣ እንድሁም በኤሌክትሪክ የሚረዱ ብስክሌቶች እንደ ሴግወይ፣ ሆቨርቦርድ፣ ሞኖ ፓቲነና ሞኖ ዊል፡ መግዣ።

ይህ ቫውቸር ለኣንድ ግዜ ብቻ የሚጠየቅ ሆኖ ከተጠቀሱት ለኣንዱ መግዣ ይውላል።


JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Buono Acquisto Biciclette

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Buono Acquisto Biciclette

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Buono Acquisto Biciclette

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Buono Acquisto Biciclette

ለሽርሽር ጉርሻ

በሪፓርቲ ኢታልያ የጸደቀው ሕግ ተከትሎ፡ በ 2020 ገቢ መመዘኛው (ISEE) ከ 40.000 ዩሮ የማይበልጥ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች በተያያዘ፡ በኣገር ውስጥ በሚገኙ የቱሪስቱ መዝናኛዎችና ኣልጋና ቁርስ የሚሰጡ የንግድ ኣግሪቱሪዝሞች (bed & breakfast) ለሚከፈሉ ክፍያዎች ድጎማ ይሰጣል።

ለእያንዳንዱ ቤተሰብ የሚሰጥ ድጎማ፡ በኣንድ የቤተሰቡ ኣባል ብቻ የሚከናወን ሆኖ እስከ 500.00 ዩሮ ይደርሳል። ድጎማው የቤተሰቡ ኣባላት ሲቀንስ፡ ይቀንሳል። በዚህም ምክንያት፡ ሁለት ሰው የያዘ ቤተሰብ የ 300.00 ዩሮ ድጎማ ሲሰጠው፡ ብቻውን ለሆነ ደግሞ 150.00 ዩሮ ይሰጣል።

1) ወጪው በኣንድ መፍትሔ ብቻ መሆን ኣለበት፡ ማለት፦ በኣንድ ኣግሪቱሪዝም ወይም ቤድ ኤንድ ብሬክፋስት ኣገልግሎት ሰጪ መሆ ኣለበት;

2) የወጪው ጠቅላላ ሰነድ በኤሌክትሮኒክ ፋክቱር ወይም የንግድ ደረሰኝ ከተጠቃሚው ፊስካል ኾድ የተያያዘ መሆን ኣለበት;

3) የኣገልግሎቱ ክፍያ፡ ያለ የቱሪዝም ኤጀንሲያዎችና ያለ ኤሌክትሮኒክ ድረገጽ ኣገልግሎት ሰጪዎች መከናወን ኣለበት።

ድጎማው ጥቅም ላይ መዋል የሚችለው በቅናሽ መጠን ላይ ፹% ያህል የሚሆነው ብቻ ሲሆን ቀሪው ፳% ደግሞ በተቀባዩየግብር ተመላሽ የሚታወቅ ነው።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ።

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Bonus vacanze

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Bonus vacanze

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Bonus vacanze

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Bonus Vacanze

ለኣደጋ ግዜ የመልሶማቋቋምያ ገቢ ውሳኔ (Rem)

የኣደጋ ግዜ መልሶ መቋቋም ገቢ፡ በኮቪድ - 19 ድንገተና ኣደጋ ምክንያት ለቤተሰብ የሚደረግ የገቢ ድጋፍ ልኬት ነው። ይህ የገቢ ድጋፍ ሁለት ኮታዎች ያሉት ሲሆን እያንዳንዳቸው ከ 400.00 እስከ 800.00 ዩሮ ነው። ለዚህ ኣስፈላጊ መስፈርቶች፡ በጣልያን ነዋሪ መሆን፣ የንብረትና የገቢ መመዘኛዎች መለክያ (ISEE) ከ 15000.00 በታች ሲሆን ነው። መልሶ ማቋቋሙ፡ ከኮቪድ - 19 ድንገተኛ ሁኔታ ቦኃላ በመንግስት ከሚሰጡት ሌሎች እውቅናዎች ጋር ግኑኝነት የለውም። በተጨማሪ በቀጥታ ወይም በሌላ መንገድ ጡሮታ ከሚያገኙ (ከተለመደው ለኣካል ጉዳተኞች ከሚሰጠው በስተቀር)፣ ተቀጥረው የሚሰሩ ጠቅላላ ገቢያቸው ከተወሰነ ግምት ከፍ ያለ ከሆነ፣ የዜግነት ድጎማ ለሚያገኙ የቤተሰብ ኣካላት ተኳሃኝ ኣይደለም።

የኣደጋ ግዜ ገቢ ወይ ድጎማ ማመልከቻዎች እስከ ሰኔ 2020 ድረስ መቅረብ ኣለባቸው።

ለተጨማሪ መረጃ የኢንፕስ ድረገጽ ይመልከቱ፣ ፓትሮናቶ ያነጋግሩ ወይም ወደ ኣርቺ የነጻ የስልክ ቁጥር ይደውሉ።.

 

የመልሶ ማቋቋም ውሳኔ፡ ለሰራተኞች ኣዲስ እውቅና 

የመልሶ ማቋቋሙ ውሳኔ፡ የኮቪድ - 19 ድንገተኛ ኣደጋን ተከትሎ፡ ለሰራተኞች የሚሰጠው ካሳ ኣሳድሶ ኣካትተዋል:

  • በማርች ወር የ 600.00 ዩሮ እውቅና ያገኙ ነጻ ባለሙያዎች፣ ቀጣይ የስራ ውል ያላቸው፣ በግላቸው የሚሰሩ በልዩ መዝገብ የተመዘገቡ፣ ወቅታዊ የቱሪዝም ሰራተኞች፡ ኣሁንም ለኣፕሪል ወር የ 600.00 ዩሮ እውቅና ያገናሉ ወይም ይቀበላሉ።
  • በግብርና የሚሰሩ ሰራተኞች ለማርች ወር የ 600.00 ይሮ እውቅና ያገኙ፡ ለኣፕሪል 2020 የ 500.00 ዩሮ እውቅና ያገኛሉ።.
  • ነጻ ባለሙያዎች በ 2020 የሁለት ወር ገቢያቸው፡ ከ 2019 የሁለት ወር ገቢው ቢያንስ ከ 33% ከቀነሰ፡ ለመይ ወር የ 1000.00 ዩሮ እውቅና ያገኛሉ። ቀጣይ የስራ ውል ያላቸውና (CO.CO.CO)፣ በተለየ መዝገብ የተመዘገቡ ሰራተኞች ለመይ ወር የ 1000.00 ዩሮ እውቅና ያገኛሉ።
  • በቱሪዝም ዘርፍ ከ 1 ጀንዋሪ 2019 እስከ 17 ማርች 2020 ይሰሩ የነበሩና ያለፍላጎታቸው ስራውን ያቋረጡ ሰራተኞች ለመይ 2020 የ 1000.00 ዩሮ እውቅና ያገኛሉ።.
  • በኮቪድ - 19 ወረርሽን የተነሳ ስራቸውን ያቋረጡ ወይም የቀነሱ የተለያዩ ቅጥር ሰራተኞችና በግላቸው የሚሰሩ ሰራተኞች፡ ለኣፕሪልና መይ ወራት የ 600.00 ዩሮ ክፍያ ያገናሉ። (ከነዚህም ከቱሪዝም የተለየ ግዝያዊ ስራ ለሚሰሩና ተለዋዋጭ ስራ ለሚሰሩ)
  • የቤት ውስጥ ሰራተኞች፡ ለኣፕሪልና ለመይ ወራት ለእያንዳንዱ ወር የ 500 ይሮ ክፍያ ያገኛሉ።ኣንድ ወይም ከኣንድ በላይ ኮንትራት ያላቸውና በሳምንት ለኣስር ሰኣታት የሚሰሩና ከኣሰሪያቸው ጋር የማይኖሩ ከሆነ።.

ኣስፈላጊ፡ ለማርች ወር የ 600.00 ይሮ ድጋፍ ያልጠየቀ ሁሉ ኣዋጁ በታተመበት በ 15 ቀናት ውስጥ ማመልከት ኣለበት። ካላመለከተ ወደ ፓትሮናቶ ጽሕፈት ቤት ይሂድ ወይም የኢንፕስ ድረገጽ ይመልከት።.

ሁሉም መታወቅያዎች ለገቢው ዕውቅና ኣይሰጡም። እውቅና የማግኘቱ ወይም የመገለሉ ወይም እውቅና ለማግኘት እንዴት እንደሚጠየቅ የበለተ መረጃ ለማግኘት፡ ለኣርቺ የነጻ ቁጥር ደውል፣ የኢንፕስ ድረገጽ ተመልከት ወይም ወደ ፓትሮናቶ ሂድ።.

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ ወይም የነጻ ክፍያ ቁጥር 800905570 ይደውሉ።

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Il Decreto Rilancio e il reddito di emergenza

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Il Decreto Rilancio e il reddito di emergenza

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Il Decreto Rilancio e il reddito di emergenza

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Il Decreto Rilancio e il reddito di emergenza

Buoni spesa

ለምግብና ለመሰረታዊ ፍላጎቶች ግዥ የቫውቸር ግብይት፡ ኢኮኖሚያዊ ችግር ላጋጠማቸው ግለሰቦችና ቤተሰቦች ቅድሚያ የሚሰጥ

-- በቁጥር 685 (ordinanza n. 658) ከሲቪል ጥበቃ መምርያ ባለስልጣን የወጣው ትእዛዝ መሰረት፤ ሁሉም የጣሊያን ማዘጋጃ ቤቶች ለተቸገሩ ሰዎች የተመደቡትን ገንዘብ ተቀብለዋል፡እነዚህ በምግብ እና በመሰረታዊ ፍላጎቶች ግብይት ላይ ሊውሉ የሚችሉ ቫውቸሮች ናቸው።

የእያንዳንዱ ማዘጋጃ ቤት የሚያገኘው የመስፈርቱንና የድጎማውን መጠን ይለያያል። ተጠቃሚዎች በኮቪድ 19 ድንገተኛ አደጋ ኢኮኖሚያዊ ተፅእኖ በጣም ለተጠቁ ሰዎች ሲሆን፡ ሌሎች ድጋፍ ለማያገኙም ቅድሚያ ይሰጣሉ ፡ ሌሎች ድጋፍ ማለት እንደ፦ (Reddito di Cittadinanza, REI, NASPI, cassa integrazione, ecc.)

በሕግ ድንጋጌ 251/2007 አንቀጽ 27 አንቀጽ1 መሰረት ፣ የዓለም አቀፍ ጥበቃ እውቅና ያገኙ ስደተኞች (ስታቱስ ዲ ሪፉጃቶ) ቫውቸሮችን በማግኘት ረገድ እንደ ጣሊያን ዜጎች ተመሳሳይ እንክብካቤ የማግኘት መብት አላቸው ፡፡

ድጎማውን ለማግኝት፡ የኣሰራሩ ሂደትና የግዜ ገደቡን ለማወቅ፡ በምት ኖሩበት ማዛጋጃ ቤት ድረገጽ ላይ ያለውን መመርያ ተከተሉ።

ሰነዶች

የቪዲዮ

ፖድካስት

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ