ጥገኝነት እና ኢሚግሬሽን

በጣልያን የተከሰተው የኮረና ቫይረስ ወረርሺን ( ኮቪድ 19): ጥገኝነት በሚጠይቁ፣ በሰነድ ወይም በመኖርያ ፈቃድ ኣሰራር ላይ እንቅፋት ኣስከትለዋል። በዚህ ክፍል በየግዜው ኣዳዲስ መረጃዎች ይወጣሉ።

የመታወቅያ ወረቀት ሰነዶች ኣገልግሎታቸው እስከ 31/12/2020 ተራዘመ

የመታወቅያ ወረቀት ሰነዶች ኣገልግሎታቸው እስከ 31/12/2020 ተራዘመ
ከ 18 ማርች 2020 ቦኋላ የወደቁ ወይም ሊወድቁ የተቃረቡ ከጣልያን መንግስት የተሰጡ የመታወቅያ ወረቀት ሰነዶች ኣገልግሎታቸው እስከ 31/12/2020 ተራዝመዋል። ከጣልያን ውጭ ለመጓዝ የሚያገለግለው ግን በመታወቅያው ያለው ቀን ብቻ ነው።


JumaMap – COVID-19 in Italy · Pidgin english Proroga Documenti 31 Dicembre
JumaMap – COVID-19 in Italy · Bambara Proroga Documenti Di Riconoscimento al 31 dicembre

ማሳሰብያ የስራ ውሉ ቀን ተራዘመ

የኣዲሱ የስራ ውል ጥያቄዎች ማቅረብያ የግዜ ገደብ ተራዘመ፡ ጁላይ 15 የነበረው ወደ ኦገስት 15 - 2020 ድረስ ተራዝመዋል።
ስለ አሠራሩ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን ጽሑፍ ያንብቡ። questo articolo.

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Proroga Regolarizzazione
JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Proroga regolarizzazione

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Proroga Regolarizzazione

ሕገ ወጥ የስራ ስምሪቶች ሕጋዊ ማድረግ


ማሳሰብያ የስራ ውሉ ቀን ተራዘመ (Proroga Regolarizzazione)
የኣዲሱ የስራ ውል ጥያቄዎች ማቅረብያ የግዜ ገደብ ተራዘመ፡ ጁላይ 15 የነበረው ወደ ኦገስት 15 - 2020 ድረስ ተራዝመዋል።

ከ 1 ጁን 2020 እስከ 15 ጁላይ 2020 ድረስ ሕገ ወጥ የስራ ግንኙነት እንዳይቀጥል ለማበረታታት የመኖርያ ፈቃድ (ፐርሜሶ ዲ ሶጆርኖ) ባልተለመደ መልኩ መጠየቅ ይቻላል። ውሉ መጠየቅ የሚቻለው ለ፦

  • ሀ) እርሻ፣ እርባታ፤ ኣሳ ማጥመድና ተመሳሳይ ስራዎች
  • ለ) ለግለሰብ ድጋፍ ስራ
  • ሐ) የቤተሰብ ፍላጎት ለማሟላት፡ የቤት ስራ.

ማመልከቻ ማስገባት የሚችሉ፦

  1. ኣሰሪዎች በጣልያን ውስጥ የሚገኙትን የውጭ ዜጎች ለመቅጠር ማመልከት ወይም መደበኛ ያልሆነ የስራ ግንኙነት በመኖሩ ኣሁንም በሂደት ያለውን የስራ ስምሪቱ ሕጋዊ ለማድረግ ማመልከት። የውጭ ኣገር ዜጎቹ ፎቶግራፋቸውና ኣሻራቸው የተወሰደላቸው ወይም ከማርች 8 በፊት ጣልያን ውስጥ የነበሩና ከዚህ ቀን ቦኃላ ጣልያን ኣገር ለቀው ያልወጡ መሆን ኣለባቸው።
  2. የውጭ ኣገር ዜጎች ከ 31 ኦክቶቨር 2019 ጀምሮ የወደቀ መኖርያ ፈቃድ ካላቸው፣ ያልታደሰ ወይም ወደ ሌላ ዓይነት ፈቃድ ካልቀየሩ፡ በጣልያን ውስጥ ለ 6 ወር የሚያገለግል ግዝያዊ መኖርያ ፈቃድ መጠየቅ ይችላሉ። የሚያመለክቱት የውጭ ዜጎች እስከ 8 ማርች በጣልያን ግዛት የነበሩና ከላይ የተጠቀሱትን የስራ ዓይነት ስራዎች የሰሩ መሆን ኣለባቸው። የውጭ ዜጎቹ በሚያገኙት የስድስት ወር መኖርያ ፈቃድ፡ የስራ ቅጥር ውል ከተፈራረሙ ቦኃላ፡ መኖርያ ፈቃዱ ወደ ስራ መኖርያ ፈቃድ ይቀየርላቸዋል። (በግብርና፣ በዓሳ ማጥመድ፣ በእርባታ፣ በግል ድጋፍ ወይም በቤት ውስጥ ስራ) ውል ከተፈራረሙ።

የሚያመለክቱት የውጭ ዜጎች እስከ 8 ማርች በጣልያን ግዛት የነበሩና ከላይ የተጠቀሱትን የስራ ዓይነት ስራዎች የሰሩ መሆን ኣለባቸው።

የውጭ ዜጎቹ በሚያገኙት የስድስት ወር መኖርያ ፈቃድ፡ የስራ ቅጥር ውል ከተፈራረሙ ቦኃላ፡ መኖርያ ፈቃዱ ወደ ስራ መኖርያ ፈቃድ ይቀየርላቸዋል። (በግብርና፣ በዓሳ ማጥመድ፣ በእርባታ፣ በግል ድጋፍ ወይም በቤት ውስጥ ስራ) ውል ከተፈራረሙ።

ማመልከቻው ተቀባይነት የማይኖረው፦

  1. 1 ስፖርቴሎ ኡኒኮ
  2. 2 ኴስቱራ ወይም በፖሊስ ኢሚግረሽን ጽሕፈት ቤት፡ የመኖርያ ፈቃዱን ለማግኘት. 

የስራ ስምሪቱ ሂደት ለማስተካከል፡ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የ 500 ዩሮ ክፍያ ግብር ከኩንባኛዎቹ ይከፈላል። ጥያቄው ከውጭ ዜጎች ከሆነ ግን ክፍያው የ 160 ዩሮ ነው።

ማመልከቻው ተቀባይነት የማይኖረው፦

ባለፉት ኣምስት ኣመታት ሕገ ወጥ ስደትን በመርዳት ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ኣሰሪ፣ በሕገ ወጥ ድርጊቶችና በኣመንዝራነት የሚያሳትፉ፣ ለኣካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በመቅጠር፣ በሕገ ወጥ ጣልቃ ገብነትና ጉልበት በመበዝበዝ ወንጀለኞች ለሆኑ ኣሰሪዎች።

ኣሰሪው በስፖተሎ ኡኒኮ የስራ ውል ካልተፈራረመ ወይም የውጭ ዜጋውን ካልቀጠረ።

ከጣልያን እንዲወጡ የተወሰነላቸው ወይም ወደ ክልሉ እንዳይገቡ የተከለከሉ፣ ወንጀል ሰርተው ለተቀጡ፣ ኣደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ፣ ሕገ ወጥ የውጭ ዜጎች እንቅስቃሴ ወይም ሌሎች ተዛማጅ ወንጀሎች የፈጸሙ፣ የሰዎች ነጻነት በመገደብ ወደ ሴተኛ ኣዳሪነት የሚያሰማሩና ከዕድሜ በታች ለሆኑ ሕፃናት ከሕግ ውጭ የሚያሰሩ የውጭ ዜጎች፡ ፍርዳቸው ባያልቅም ተቀባይነት የላቸውም።

ማነናውም ጥፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት በስርዓቱ ላይ እንደ ስጋት የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች ተቀባይነት የላቸውም።

ይህ ድንጋጌ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ በኣሰሪውና በሰራተኛው ላይ ያሉ የወንጀልና የኣስተዳደራዊ ሂደቶች ይታገዳሉ፡ እነሱም፦

  1. የሰራተኛው የስራ ቅጥር ማመልከቻ ካቀረቡ
  2. በሕገወጥ ለገቡና ትክክለኛ የመኖርያ ፈቃድ ለሌላቸው

ማመልከቻ ገብቶ ኣሰራሩ በሂደት ላይ እያለ፡ የውጭ ዜጋው በከባድ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሊባረር ኣይችልም።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ ወይም የነጻ ክፍያ ቁጥር 800905570 ይደውሉ።Your Website Title
Ero Straniero

Ero Straniero FacebookJumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Regolarizzazione ed emersione rapporti di lavoro

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Regolarizzazione ed emersione rapporti di lavoro

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Regolarizzazione ed emersione rapporti di lavoro

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Regolarizzazione ed emersione rapporti di lavoro

በኮቪድ 19 የኣደጋ ግዜና የኣለም ኣቀፍ ጥበቃ እውቅና ኣሰጣጥ፡ ኣሰራር

የኮቪድ 19 ቫይረስ መስፋፋት በጣልያንና በኣለም ድንገተኛ ኣደጋ ነው

የሁላችንም ጤንነት ለማስጠበቅ ከምንኖርበት ቦታ ኣለመውጣት ነው። መውጣት ወይም መንቀሳቀስ ያለብን፡ ለስራ ኣስፈላጊነት፣ ለኣስፈላጊ ሁኔታዎች፣ በጤና ምክንያትና ወደ መኖርያችን ለመመለስ ብቻ መሆን ኣለበት።

ከነዚህ ውጪ ሲንቀሳቀስ የተገኘ፡ እንዲቀጣ ተወስነዋል።

የቫይረሱ መስፋፋት ለማስቆም፡ በኣለም ኣቀፉ ጥበቃ እውቅና ኣሰራር ላይ፡ በኣንዳንድ ገጽታዎች ተጽዕኖ የሚያሳድሩ እርምጃዎች ተወስደዋል።

3. ለኣለም ኣቀፍ ጥበቃ የጥገኝነት ጥያቄ ማመልከት ትፈልጋለህ?

የፖሊስ ደህንነት ጽ/ቤት (ኡፊቾ ኢሚግራ ስዮነ) ለህዝብ ዝግ ነው። የጥገኝነት ጥያቄ ፍላጎትህን ለማመልከት ግን ወደ ፖሊስ ጽ/ ቤት (ኴስቱራ) መሄድ ትችላለህ። ጥያቄህን በተቻለ ግዜ ይመዘገባል።

2. ከክልሉ ኮምሽን ለቃለ መጠይቅ ጥሪ ትጠብቃለህ ወይም የቃለ መጠይቁ ቀን በዚህ ቀናት ነበር?

የቫይረሱ መስፋፋት ለመከላለል፡ በዚህ ወቅት የክልል ጽ/ቤት ኮምሽኖች ዝግ ናቸው መጠየቅም ኣቋርጠዋል። ይህንን ድንገተኛ ኣደጋ እንደተጠናቀቀ በተመዘገብከው መሰረት ኮምሽኑ ለቃለ መጠይቅ ኣዲስ ቀጠሮ ይሰጠሃል።

ማስታወስ ያለብህ፡ ከኮምሽኑና ከመንግስት ጽ/ቤቶች የሚላኩልህ ማንኛውም መልእክቶች፡ ባሳወቅካቸው የመጨረሻ ኣድራሻህን ነው። ከፕሮጀክት ወይም ከመጠለያ ውጭ ከሆንክ፡ በምትኖርበት የቤት ደወል ስር ስምህን በደንብ እንደተጻፈ ኣረጋግጥ።

3. ለኣለም ኣቀፍ ጥበቃ ያቀረብከውን ጥያቄ፡ መልስ እየተጠባበቅክ ነው?

መልሱ በተዘጋጀ ግዜ፡ መልእክት ከነመልሱ ይደርሰሃል።

በነዚህ ቀናት ውስጥ ውጤቱን ከተቀበልክና የኣለም ኣቀፍ ጥበቃ ጥያቀህ እውቅና ካገኘህ፡ የድንገተኛ ኣደጋውን እንዳበቃ ወደ ፖሊስ (ኴስቱራ) በመሄድ የመኖርያ ፈቃድህን መጠየቅ ኣለብህ።

ውሳኔው ደርሶህ በውሳኔው ካልረካህና ይግባኝ ማለት ከፈለግክ፡ ማወቅ ያለብህ ኣሁን በድንገተኛ ኣደጋው በተፈጠሩ ችግሮች ምክንያት የይግባኙ ቀን ገደብ ለግዜው ቆመዋል። ስለዚህ ይግባኙ ለማቅረብ ግዜ ኣለህ። ለማንኛውም በ ኢ-መይል ወይም በስልክ ከጠበቃህ ግንኙነት ማድረግ ትችላለህ። በ መጠለያ ወይም በፕሮጀክት ከሆንክ ደግሞ ከፕሮጀክቱ ህግ ኣማካሪ ግንኙነት ኣድርግ።

4. መርጃዎች ያስፈልጉሃል ወይም ወደ ኮምሽኑ የምትልካቸው ሰነዶች ኣሉ?

በዚህ ግዜ የኮምሽኑ ጽ/ቤት ለህዝብ ዝግ ናቸው፡ በማንኛውም ግዜ ግን ለሚመለከተው ኮምሽን ኢ- መይል መላክ ትችላለህ። ቀጥሎ የተያያዙት መገናኛዎች ተመልከት

የመኖርያ ፈቃድ ወይም ፐርሜሶ ዲ ሶጆርኖ የሚያገለግለው ግዜ

የ “ኩራታሊያ” የሕግ ድንጋጌ ከተቀየረ በኋላ ሁሉም የመኖሪያ ፈቃዶች እስከ ኦገስት 30 ቀን 2020 ድረስ እንደሚጸኑ እናሳውቅዎታለን ፡፡ 31 agosto 2020.

የመታወቂያ ሰነዶች ማራዘሚያ

Aggiornamento 17/08/2020
La validità dei documenti di riconoscimento e di identità è stata prorogata al 31 dicembre 2020.

ሁሉም በጣልያን መንግስት እውቅና የተሰጣቸው መታወቅያ ወረቀቶች፡ የወደቁ ወይም የመውደቅያ ግዝያቸው እስከ 18 ማርች 2020 የሆኑ መታወቅያዎች የመውደቅያ ግዝያቸው እስከ 31 ኦገስት 2020 ተራዝመዋል። ለውጭ ለሚደረግ ጉዞ የሚያገለግለው ግን በመታወቅያው ያለው ቀን ብቻ ነው። (Art. 104 Dl Cura Italia)
የመታወቅያ ወረቀት ሰነዶች የትኞቹ ናቸው?
የመታወቅያ ወረቀት
እንደ መታወቅያ ወረቀት ተመሳሳይ ኣገልግሎት ያላቸው የሚባሉት መታወቅያዎች፦ ፓስፖርት፣ የመኪና መንጃ ፈቃድ፣ የባሕር መንጃ ፈቃድ፣ የጥሮታ መታወቅያ፣ የመሳርያ ፈቃድ ሁሉም ስእልና ማሕተም ወይም ሌላ ተመሳሳይ ምልክት ያላቸው፡ ከመንግስት መስርያ ቤቶች የሚተሰጡ ናቸው።

የኢሚግሬሽን ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት - የመኖሪያ ፈቃድ ፣ የፖሊስ መሥሪያ ቤት ተጠርቷል

ማስታወቂያ - የመኖሪያ ፈቃዶች ፣ የ ‹QUESTURA CONVOCATIONS› ላክ
የሕጉን ድንጋጌ በመከተል n. ለመኖሪያ ሰነዶች የሚያመለክቱ ማመልከቻዎች በሚያቀርቡበት ጊዜ ለተቀበሉት የፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት የቀረበው ጥሪ ለሌላ ጊዜ ሊለጠፍ እና ማንኛውም አዲስ ቀን በኤስኤምኤስ አማካይነት ይገለጻል ፡፡ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከመሄዳችን በፊት ‹የኢሚግሬሽን ፖርታል› ን እንዲያማክሩ እንመክራለን - https://www.portaleimmigrazione.it/ጥያቄውን ለማቅረብ ፣ የስብሰባውን ቀን ለማጣራት Sportello አሚኮ ፖስታ ቤት በተቀበለው የተጠቃሚ ስም እና የይለፍ ቃል በማረጋገጥ ፡፡

ማስታወቂያ - የስምምነት ቢሮክክር ልዩነቶች

INFO ለፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት የእድሳት እና የመኖሪያ ፈቃዶች ጉዳይ ለጊዜው ለሕዝብ ዝግ ናቸው ፡፡
ለአለም አቀፍ ጥበቃ (የጥገኝነት ማመልከቻ) ማመልከቻ ለማስገባት ማመልከቻ የሚያስገቡ ቆጣሪዎች ብቻ ናቸው ክፍት ናቸው ፡፡

ምንጭ-የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሰነዶች

የቪዲዮ

ፖድካስት

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ