ሥራ

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) የድንገተኛ ግዜ ምክንያት መዘጋት ወይም ማቆም የሚያስከትለው ጉዳት ለመቋቋም፡ የጣልያን መንግስት፡ ሰራተኞችና የንግድ ስራዎችን የሚደግፉ ተከታታይ እርምጃዎችን ተግባራዊ ኣድርገዋል። በዚህ ገጽ በየግዜው፡ በስራ ላይና በስልጠና ላይ ከጸደቁ ሕጎች ጋር የሚዛመዱ ሁሉም ዝርዝሮችና፡ ለድጎማ የማመልከት ሂደቶችን በሚመለከት መረጃውን በየግዜው እያደሰ ያቀርባል።

ማሳሰብያ የስራ ውሉ ቀን ተራዘመ

የኣዲሱ የስራ ውል ጥያቄዎች ማቅረብያ የግዜ ገደብ ተራዘመ፡ ጁላይ 15 የነበረው ወደ ኦገስት 15 - 2020 ድረስ ተራዝመዋል።
ስለ አሠራሩ የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን ጽሑፍ ያንብቡ። questo articolo.

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Proroga Regolarizzazione
JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Proroga regolarizzazione

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Proroga Regolarizzazione

መብት በመስመር - ኑሜሮ ቬርደ ለወጣው የስራ ውል ማስተካከያ (Regolarizzazione)

800 999 977

ኣርቺ፡ ስለ ወጣው የስራ ውል ማስተካከያ በኑሜሮ ቬርድ መልስ ይሰጣል፡፡

ለስራ ውሉ ማስተካከያ በሚመለከት ይህ የመብት መስመር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ 9.00 – 13.00 እና ከ 14.30 – 18.30 ድረስ ይመልሳል፡፡ ነፃ የመብት መስመር ቁጥር በአሁኑ ወቅት በግብርና ወይም በግል እንክብካቤ አገልግሎቶች ውስጥ ለሚሰሩ፡ ስለ ስራ ውሉ አዳዲስ የአሠራር ህጎች መረጃ ለሚጠይቁ መልስ ይሰጣል ፡፡

ኣርቺ - በክልል ኮሚቴዎች አማካይነት አስፈላጊ መስፈርቶችን ላሟሉ ሁሉም የውጭ ዜጎች የሕግ ማዕቀፍ የማግኘት ዕድልን ይከተላል ፣ ይቆጣጠራል ፡፡ የመብት መስመሩ በጁማማፕ አውታረመረብ አገልግሎቶች በመጠቀም ማንኛውንም ሪፖርት የተደረጉ ማጭበርበሮችንና አድሎአዊ አሰራሮችን ይከሳል።

አገልግሎቱ ከመስመር ስልክና ከሞባይል ስልኮች ነፃ ሲሆን የአርቺ አውታረ መረብ የቋንቋ ኣስተርጓሚዎችን ይጠቀማል።

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] SOS DIRITTI 800 999 977

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] SOS DIRITTI 800 999 977

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] SOS DIRITTI 800 999 977

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] SOS DIRITTI 800 999 977

ስራ በማቆም ምክንያት ለሚከፈሉ ልዩ ፈቃድ

ኮቪድ - 19፡ ስራ በማቆም ምክንያት ለሚከፈላቸው ማራዘምና ተጨማሪ ግዜ መስጠት

በኮቭድ - 19: ከ 23 ፈብርዋሪ እስከ 31 ኦገስት 2020 ስራ በማቆም ይከፈላቸው የነበረ ተጨማሪ 5 ሳምንታት ልዩ የዕረፍት ግዜ ይሰጣቸዋል። ይህ ለነበረው 9 ሳምንታት ተጨማሪ ማራዘምያ የሚጠቀሙበት ነው። ተጨማሪ የ 4 ሳምንታት ግዜ ከ 1 ሰፕተምበር እስከ 31 ኦክቶቨር 2020 ጥቅም ላይ ሊውል ይችላል። በቱሪዝም፣ በንግድ፣ በትልልቅ ስብሰባዎች፣ በመዝናኛ ፓርኮች፣ የቀጥታ ትርኢትና በሲነማ ላሉት ሰራተኞች፡ እነዚህ 4 ሳምንታት ከሰፕተምበር 1 በፊት መጀመር ይችላሉ።

ከ 12 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት ላሉዋቸው ወላጆች፡ ከዚህ ቀደም ከታቀዱት 15 ቀናት ተጭማሪ ከ 5 ማርች እስከ 31 ጁላይ 2020 ልዩ የዕረፍት ቀናቱ ወደ 30 ቀናት ይራዘማል። በግል ስራ ተቀጥረው ለሚሰሩ ለልዩ ዕረፍቱ 50% ይከፈላቸዋል። የሕፃናት መዋያ ካልጠየቁና ሌላው ወላጅ ስራ ኣጥ ካልሆነ፣ ሰራተኛ ያልሆነ ወይም የገቢ ድጋፍ መሳርያዎች ተቀባይ ካልሆነ ልዩ ዕረፍቱ መጠየቅ ይችላል።

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Covid-19: cassa integrazione e congedo

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Covid-19: cassa integrazione e congedo

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Covid-19: cassa integrazione e congedo

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Covid-19: cassa integrazione e congedo

ስራን በሃላፊነት ማከናወን

እስከ የኮቪድ 19 የድንገተኛ ጊዜ ማብቂያ ድረስ ፣ ቢያንስ አንድ ልጅ ከ 14 ዓመት በታች ላላቸው፡ የግል ሴክተር ሠራተኞች፡ ከሥራው የራሱ ባህሪዎች ጋር የሚጣጣም እስከሆነ ድረስ ባሉበት ሥራውን የማከናወን መብት አላቸው። ስራ ያቆሙ ወይም ሥራ በሚቋረጥበት ጊዜ የገቢ ድጋፍ መሳሪያዎችን የሚቀበል በቤተሰብ ውስጥ ሌላ ወላጅ ሊኖር አይገባም፡፡ በተጨማሪም፡ በቤተሰብ ውስጥ የማይሠራ ሌላ ወላጅ ካለ ፣ ይህን ዓይነት ሥራን መቀበል አይቻልም። ስራውን ለማከናወን የሚያስችሉ የኤለክትሮኒክ መሳርያዎች (ለምሳሌ ኮምፒተር) ከኣሰሪው ካልቀረቡ ሰራተኛው ባለው መሳርያ መጠቀም ይችላል።

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Lavoro Agile

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Lavoro Agile

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Lavoro Agile

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Lavoro Agile

ለኤኮኖሚያዊ እንቅስቅሴዎች ድጎማ

የሪፓርት ኢታልያ ድንጋጌ፡ በንግድ፣ በግል ስራ፣ በግብር ለሚተዳደሩ ወይም እስከ 31 ማርች 2020 ያልተዘጋ የንግድ ፈቃድ ላላቸው፡ ተመላሽ የማይሆን የገንዘብ ድጎማ እንዲያገኙ እውቅና ሰጥተዋል። 

ይህ ድጎማ የሚሰጣቸው በኣፕሪል 2020 ያስመዘገቡት ደረሰኝ፡ በኣፕሪል 2019 ካስመዘገቡት ሁለት ሰወስተኛው የቀነሰ ሲሆን ነው። ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ባይኖራቸውም ከ 1 ጀንዋሪ 2019 እንቅስቃሴ ለጀመሩም ድጎማ ይፈቀድላቸዋል።

በማንኛውም ሁኔታ መጠኑ ከ 1000 ዩሮ በታች እንዳይሆን ተወስነዋል ፦

 1. 1. 20% - በኣፕሪል 2020 እና በኣፕሪል 2019 መካከል ያለውን የመጨረሻው የገቢ ግብር ልዩነት ከ 400.000 ዩሮ የማይበልጥ ከሆነ
 2. 2. 15% - በኣፕሪል 2020 እና በኣፕሪል 2019 መካከል ያለውን የመጨረሻው የገቢ ግብር ልዩነት ከ 400.000 ዩሮ የሚበልጥከሆነ
 3. 3. 10% - በኣፕሪል 2020 እና በኣፕሪል 2019 መካከል ያለውን የመጨረሻው የገቢ ግብር ልዩነት ከ 1 ሚልየን ዩሮ የሚበልጥ ከሆነና ከ 5 ሚልየን ዩሮ ያነሰ ከሆነ

ይህ ተመላሽ የማይሆነው ድጎማ ለማግኘት ፍላጎት ያላቸው ወገኖች ማመልከቻውን በኤለክትሮኒ መንገድ ለገቢዎች ኤጀንሲ (ኣጀንስያ ዴለ ኤንትራተ) ያቀርባሉ። ይህን ለማቅረብ ኣስፈጽሚዎች እንዲያስፈጽሙላቸው ውክልና መስጠት ይችላሉ።.  

በጁማማፕ በተጠቀሱት የፓትሮናቶ፣ የሰራተኞች ማሕበር ወይም የሕግና የኣስተዳደር እርዳታ ወደሚሰጡ ጽሕፈት ቤቶች እንዲሄዱ እንመክርዎታለን። 

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ።

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Contributo per le attività economiche

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Contributo per le attività economiche

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Contributo per le attività economiche

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Contributo per le attività economiche

ለኪራዮች ድጋፍ

የሪፓርቲ ኢታልያ ሕግ ከጸደቀ ቦኃላ በንግድ፣ በስነጥበብ ወይም በሙያ ላይ ለተያያዙ ርእሰ ጉዳዮች በሚመለከት ከ 5 ሚልዮን ዩሮ የማይበልጥ ገቢ ላላቸው የሚጠብቁት፦

ለመኖርያ ሳይሆን ለኢንዱስትሪ፣ ለንግድ፣ ለቱሪዝም ወይም ለግል ባለሙያዎች እንቅስቃሴ የሚውሉ የኪራይ ቤቶች ከወርሃዊው የኪራይ ክፍያው ወደ 60% የሚጠጋ ብድር፡.

ብያንስ ኣንድ ለነዋሪነት የማይውል ቤት ጨምሮ ውስብስብ ኣገልግሎቶች ለሚሰጡ የኩንባኛዎች ውል 30% የሚጠጋ ብድር

ብድሩ፡ የሚያስመዘግቡት የስራ እንቅስቃሴ ይብዛም ይነስም ለሁሉም ሆቴሎች ነው

የ 60% ብድር የሚጠበቀው ለንግድ ነክ ኣካላት ላልሆኑ እንደ ሰወስተኛ ኣካላትና እውቅና ላገኙ የሃይማኖት ተቋማት ጭምር ነው

ብድሩ በ 2020 ለማርች ለኣፕሪልና ለመይ በተከፈለው ክፍያ መጠን ይስተካከላል። ለንግድ እንቅስቃሴ የተከራዩ ሰዎች፡ ብድሩ የሚከናወነው ካለፈው ያስመዘገቡት የገቢ መጠን ሲነጻጸር ቢያንስ ከ50% የማሽቆልቆል ወይም የመቀነስ ሁኔታ ላጋጠማቸው ነው።

በዚህ ጽህፍ ውስጥ የተሰጠው የብድር ክፍያ ኣጠቃቀም፡ ወደ ራሱ በቀጥታ ሲሆን፣ ወደ ሌሎች ከተላለፈ ወደ ሌላ የብድር ተቋም ወይም የገንዘብ ተቋማት ሊተላለፍ ይችላል። ቀጥሎ ብድሩ የሚሰጥበት ምርጫ ይሆናል።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ።

በፓትሮናቶ፣ በነጋዴዎች ማሕበር፣ በሰራተኛ ማሕበር ወይም በጁማማፕ የሕግና ኣስተዳደራዊ ድጋፍ ለሚሰጡ ጽሕፈት ቤቶች እንዲያማክሩ እንመክርዎታለን።

JumaMap – COVID-19 in Italy · [Bambara] Info Covid: agevolazioni per gli affitti

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN] Info Covid: agevolazioni per gli affitti

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Info Covid: agevolazioni per gli affitti

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Info Covid: agevolazioni per gli affitti

የእርሻ ሥራን ለማሳደግ እርምጃዎች

በግብርና ስራ መስፋፋት ላይ “ሪፓርቲ ኢታልያ” በኣንቀጽ 101 ባወጣው ሕግ ማጽደቁን ተከትሎ በግብርናው ዘርፍ የስራ እድል ለመፍጠር ከ 30 ቀናት ለማይበልጥ ውል ኣዘጋጅተዋል፡ ለተጨማሪ 30 ቀናትም ይታደሳል። እንዲሁም በዜሮ ሰዓት በካሳ ኢንተግራስዮነ ለሚገኙ፣ ከናስፒ ወይም ከዲስኮል ወይንም ከሬዲቶ ዲ ቺታዲናንሳ ድጎማ የሚያገኙም ጭምር መሳተፍ ይችላሉ። ውሉ በሚፈራረሙበት ግዜ እስከ 2000 ወሰን ያለው ለ 2020 የሚያገኙት ድጎማ ኣያቋርጥም ወይም ኣይቀንስም።.

 

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ ወይም የነጻ ክፍያ ቁጥር 800905570 ይደውሉ።

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Misure Per Promozione Del Lavoro Agricolo

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Misure Per Promozione Del Lavoro Agricolo

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Misure Per Promozione Del Lavoro Agricolo

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Misure Per Il Lavoro Agricolo

ሕገ ወጥ የስራ ስምሪቶች ሕጋዊ ማድረግ


ማሳሰብያ የስራ ውሉ ቀን ተራዘመ (Proroga Regolarizzazione)
የኣዲሱ የስራ ውል ጥያቄዎች ማቅረብያ የግዜ ገደብ ተራዘመ፡ ጁላይ 15 የነበረው ወደ ኦገስት 15 - 2020 ድረስ ተራዝመዋል።

ከ 1 ጁን 2020 እስከ 15 ጁላይ 2020 ድረስ ሕገ ወጥ የስራ ግንኙነት እንዳይቀጥል ለማበረታታት የመኖርያ ፈቃድ (ፐርሜሶ ዲ ሶጆርኖ) ባልተለመደ መልኩ መጠየቅ ይቻላል። ውሉ መጠየቅ የሚቻለው ለ፦

 • ሀ) እርሻ፣ እርባታ፤ ኣሳ ማጥመድና ተመሳሳይ ስራዎች
 • ለ) ለግለሰብ ድጋፍ ስራ
 • ሐ) የቤተሰብ ፍላጎት ለማሟላት፡ የቤት ስራ.

ማመልከቻ ማስገባት የሚችሉ፦

 1. ኣሰሪዎች በጣልያን ውስጥ የሚገኙትን የውጭ ዜጎች ለመቅጠር ማመልከት ወይም መደበኛ ያልሆነ የስራ ግንኙነት በመኖሩ ኣሁንም በሂደት ያለውን የስራ ስምሪቱ ሕጋዊ ለማድረግ ማመልከት። የውጭ ኣገር ዜጎቹ ፎቶግራፋቸውና ኣሻራቸው የተወሰደላቸው ወይም ከማርች 8 በፊት ጣልያን ውስጥ የነበሩና ከዚህ ቀን ቦኃላ ጣልያን ኣገር ለቀው ያልወጡ መሆን ኣለባቸው።
 2. የውጭ ኣገር ዜጎች ከ 31 ኦክቶቨር 2019 ጀምሮ የወደቀ መኖርያ ፈቃድ ካላቸው፣ ያልታደሰ ወይም ወደ ሌላ ዓይነት ፈቃድ ካልቀየሩ፡ በጣልያን ውስጥ ለ 6 ወር የሚያገለግል ግዝያዊ መኖርያ ፈቃድ መጠየቅ ይችላሉ። የሚያመለክቱት የውጭ ዜጎች እስከ 8 ማርች በጣልያን ግዛት የነበሩና ከላይ የተጠቀሱትን የስራ ዓይነት ስራዎች የሰሩ መሆን ኣለባቸው። የውጭ ዜጎቹ በሚያገኙት የስድስት ወር መኖርያ ፈቃድ፡ የስራ ቅጥር ውል ከተፈራረሙ ቦኃላ፡ መኖርያ ፈቃዱ ወደ ስራ መኖርያ ፈቃድ ይቀየርላቸዋል። (በግብርና፣ በዓሳ ማጥመድ፣ በእርባታ፣ በግል ድጋፍ ወይም በቤት ውስጥ ስራ) ውል ከተፈራረሙ።

የሚያመለክቱት የውጭ ዜጎች እስከ 8 ማርች በጣልያን ግዛት የነበሩና ከላይ የተጠቀሱትን የስራ ዓይነት ስራዎች የሰሩ መሆን ኣለባቸው።

የውጭ ዜጎቹ በሚያገኙት የስድስት ወር መኖርያ ፈቃድ፡ የስራ ቅጥር ውል ከተፈራረሙ ቦኃላ፡ መኖርያ ፈቃዱ ወደ ስራ መኖርያ ፈቃድ ይቀየርላቸዋል። (በግብርና፣ በዓሳ ማጥመድ፣ በእርባታ፣ በግል ድጋፍ ወይም በቤት ውስጥ ስራ) ውል ከተፈራረሙ።

ማመልከቻው ተቀባይነት የማይኖረው፦

 1. 1 ስፖርቴሎ ኡኒኮ
 2. 2 ኴስቱራ ወይም በፖሊስ ኢሚግረሽን ጽሕፈት ቤት፡ የመኖርያ ፈቃዱን ለማግኘት. 

የስራ ስምሪቱ ሂደት ለማስተካከል፡ ለእያንዳንዱ ሰራተኛ የ 500 ዩሮ ክፍያ ግብር ከኩንባኛዎቹ ይከፈላል። ጥያቄው ከውጭ ዜጎች ከሆነ ግን ክፍያው የ 160 ዩሮ ነው።

ማመልከቻው ተቀባይነት የማይኖረው፦

ባለፉት ኣምስት ኣመታት ሕገ ወጥ ስደትን በመርዳት ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ኣሰሪ፣ በሕገ ወጥ ድርጊቶችና በኣመንዝራነት የሚያሳትፉ፣ ለኣካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በመቅጠር፣ በሕገ ወጥ ጣልቃ ገብነትና ጉልበት በመበዝበዝ ወንጀለኞች ለሆኑ ኣሰሪዎች።

ኣሰሪው በስፖተሎ ኡኒኮ የስራ ውል ካልተፈራረመ ወይም የውጭ ዜጋውን ካልቀጠረ።

ከጣልያን እንዲወጡ የተወሰነላቸው ወይም ወደ ክልሉ እንዳይገቡ የተከለከሉ፣ ወንጀል ሰርተው ለተቀጡ፣ ኣደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ፣ ሕገ ወጥ የውጭ ዜጎች እንቅስቃሴ ወይም ሌሎች ተዛማጅ ወንጀሎች የፈጸሙ፣ የሰዎች ነጻነት በመገደብ ወደ ሴተኛ ኣዳሪነት የሚያሰማሩና ከዕድሜ በታች ለሆኑ ሕፃናት ከሕግ ውጭ የሚያሰሩ የውጭ ዜጎች፡ ፍርዳቸው ባያልቅም ተቀባይነት የላቸውም።

ማነናውም ጥፋት ከግምት ውስጥ በማስገባት በስርዓቱ ላይ እንደ ስጋት የሚቆጠሩ የውጭ ዜጎች ተቀባይነት የላቸውም።

ይህ ድንጋጌ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚያልቅ ድረስ በኣሰሪውና በሰራተኛው ላይ ያሉ የወንጀልና የኣስተዳደራዊ ሂደቶች ይታገዳሉ፡ እነሱም፦

 1. የሰራተኛው የስራ ቅጥር ማመልከቻ ካቀረቡ
 2. በሕገወጥ ለገቡና ትክክለኛ የመኖርያ ፈቃድ ለሌላቸው

ማመልከቻ ገብቶ ኣሰራሩ በሂደት ላይ እያለ፡ የውጭ ዜጋው በከባድ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ሊባረር ኣይችልም።

በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ያለው መረጃ፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ኣያስገባም፡ ስለሆነም ኣማካሪዎችን ይጠይቁ ወይም የነጻ ክፍያ ቁጥር 800905570 ይደውሉ።Your Website Title
Ero Straniero

Ero Straniero FacebookJumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Regolarizzazione ed emersione rapporti di lavoro

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Regolarizzazione ed emersione rapporti di lavoro

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Regolarizzazione ed emersione rapporti di lavoro

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Regolarizzazione ed emersione rapporti di lavoro

ለግብርና ስራ ምን ዓይነት ዕድሎች ኣሉ?

በኮቪድ 19 ድንገተኛ ኣደጋ ምክንያት የእርሻው ክፍል በመላው ጣልያን ወቅታዊ የሰራተኞች እጥረት እያጋጠመ ነው። ክልሎች፣ ግዛቶችና የሚመለከታቸው ማሕበራት፡ በእርሻውና በሰራተኞች መካከል: ለስራው የሚያበረታቱ በመስመር ድረግጾቻቸው እየላኩ ነው። ክልሎች፣ ግዛቶችና የንግዱ ማሕበራት፡ በእርሻዎቹና በሰራተኞቹ መካከል፡ ለስራው የሚያበረታቱ በመስመር ድረ ገጾቻቸው እየላኩ ነው። .

ለማመልከት የሚከተሉት ድረ ገጾች መጎብኘት ነው፦

ያስታውሱ፡ በሥራ ቦታ ችግር ካለብዎ ደሞዝዎ ወይም የሥራ ሰዓቱ ከስምምነቱ ጋር የማይጣጣም ከሆነ ፣ የደህንነት እርምጃዎች ካልተከበሩ ፡ ለሰራተኞች ማሕበር ወይም ለኑሜሮ ቬርደ በ 800905570 ወይም በላይካ ሞባይል መስመር ቁ. 351 1376335 ይጦቁሙ።

ምንጭ “Lavoro agricolo, le iniziative per incrociare meglio domanda e offerta”, www.integrazionemigranti.gov.it

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Lavoro in agricoltura: quali opportunità?

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Lavoro in agricoltura: quali opportunità?

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Lavoro in agricoltura: quali opportunità?

Info CuraItalia

seleziona lingua 2
Seleziona lingua:

የ600 ዩሮ ድጎማ ፤ ለጥገኝነት ፈላጊዎች ፣ ስደተኞች እና ለሌሎች የመኖሪያ ፈቃዶችም እንዲሁ ይሰጣል

ከኤፕሪል 1 ቀን 2020 INPS ድር ገጽ ውስጥ (https://www.inps.it/) የማርች ወር የ 600 ዩሮ ድጎማ ለማግኘት ማመልከት ይችላሉ ፡፡ መጠየቅ የሚችለው ማን ነው?

 • እስከ 23 ፌብርዋሪ 2020 በግላቸው የንግድ ፈቃድ (ፓርቲታ ኢቫ ያለቸው) የሰሩ የግል ባለሙያዎች

 • እስከ 23 ፈብርዋሪ በባልደረባነት በቀጣይ የሰሩ (Collaboratori coordinati e continuativi - Co.co.co.)

 • የእጅ ባለሞያዎች ፣ ነጋዴዎች ፣ ቀጥታ ገበሬዎች ፣ አከፋፋዮች እና ሰፋሪዎች

 • በቱሪዝምና በተርማል ብ 1 ጀንዋሪ 2019 እና 17 ማርች 2020 መሃል በግዚያዊ ስራ ይሰሩ የነበሩ (በራሳቸው ፈ ቃድ ባይሆንም ከስራው ያቋረጡ)

 • ኣርቲስቶች/ከያኒዎች፡ በ 2019 ብያንስ 30 ዕለታዊ ግብር የከፈሉና የያዝነው ዓመት ገብያቸው ከ 50.000 ዩሮ ያልበለጠ

 • የግብርና ሰራተኞች ፣ የጊዝያዊ ግብርና ሰራተኞች እና ሌሎች በዓመታዊው ዝርዝር ውስጥ የተካተቱት የሰራተኞች ምድቦች ቢያንስ በ 2019 ቢያንስ ከ 50 ቀናት በላይ የሰሩ

እስከ ኣሁን ደመወዝ ወይ ገቢ ያላቸው ይህን ድጎማ መጠየቅ ኣይችሉም ፦ Pensione ጡሮታ/ reddito di cittadinanza የዜግነት ገቢ /Ape sociale የ ኣፐ ማሕበራዊ ክፍያ /Assegno ordinario di invalidità የአካል ጉዳት አበል

የአሰራር ሂደቱን ለመድረስ ምን ያስፈልግዎታል?

 • INPS - ድጎማው መክፈል የሚችልበት የባንክ ሂሳብ ቁጥር

የ INPS የመስመር ላይ አገልግሎቶች መዳረሻ መግባት https://serviziweb2.inps.it/RichiestaPin/jsp/menu.jsp

የሕፃን መዋያ ድጎማ፡ እንዲሁም ለስደተኞች እና ለጥገኝነት ፈላጊዎችም ይሰጣል

በ INPS ድርጣቢያ (www.inps.it) ላይ ፣ በሌላ አማራጭ በኮንጀዶ ፋሚሊያረ፦ በጣሊያን የእንክብካቤ ህግ ውስጥ ለተሰጡ የሕፃናት እንክብካቤ አገልግሎቶች ለመክፈል ድጎማ መጠየቅ ይችላሉ ፡፡.. . .

ድጎማው ለሚቀጥሉት ሠራተኞች ይመለከታል

 • የግሉ ዘርፍ ሠራተኞች
 • ለተለየ አስተዳደር ብቻ የተመዘገበ (ጀስትዮነ ሴፓራታ)
 • በ INPS በግላቸው ለተመዘገቡ
 • በራስ ተቀጣሪነት ለተመዘገቡ ባለሙያውች

ድጎማው ለህፃናት መዋያ አገልግሎቶች የሚያወጡትን ዕድሜያቸው ከ 12 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ላለው ለእያንዳንዱ ቤተሰብ ከፍተኛው ድርሻ 600 ዩሮ ነው ፡፡ የዕድሜ ገደቡ በትምህርት ቤት ለተመዘገቡ ወይም በሕፃናት ማቆያ ማዕከላት ውስጥ ለተያዙ የአካል ጉዳተኞች ልጆች አይመለከትም ፡፡ ድጎማው በ INPS የሚከፈለው በቤተሰብ የሂሳብ ደብተር (ሊብረ) በኩል ነው። . .

መረጃ ለማግኘት እና ድጎማውን ለመጠየቅ የ INPS የመስመር ላይ አገልግሎቶችን መድረስ አለብዎት (https://www.inps.it/) ከሚከተሉት ማስረጃዎች በአንዱ በኩል dell’INPS (https://www.inps.it/)

ማስጠቀቅያ፥ ማመልከቻው በቀለለው ፒን ከተላከ ፣ በቤተሰብ የሂሳብ ደብተር ላይ ለመመዝገብ እና ድጎማው በኤሌክትሮኒክ መንገድ ለማግኘት የፒን ሁለተኛውን ክፍል ማግኘት አለበት ፡፡

ልዩ ፈቃድ ለኮቪድ 19 ፡ ለጥገኝነት ፈላጊዎችና ለስደተኞችም ይፈቅዳል

ኣብ ናይ INPS ናይ መርበብ መስመር ኣገልግሎት ( https://www.inps.it/ ) ምእታው ካብ 5 ማርች ጀሚሩ ክሳብ ዝጅመር ኩሎም ሰራሕተኛታት ን 25 መዓልታት ነዚ ፍሉይ ፍቓድ ክሓቱ ይኽእሉ።https://www.inps.it/

Caratteristiche:

- ድሜያቸው እስከ 12 ዓመት ለሆኑ ሕፃናት ወላጆች 50% ክፍያ

- ዕድሜያቸው ከ 12 እስከ 16 ዓመት ለሆኑ ሕፃናት ወላጆች ያለ ክፍያ

- ከባድ የአካል ጉዳት ላለባቸው ልጆች ወላጆች 50% ክፍያ (ያለ ዕድሜ ገደብ)

የአሰራር ሂደቱን ለመድረስ ምን ያስፈልግዎታል?

COME ACCEDERE AI SERVIZI ONLINE PER RICHIEDERE:
BONUS 600 EURO / CONGEDO STRAORDINARIO COVID / BONUS BABYSITTING

በ INPS የመስመር ላይ ኣገልግሎት ከሚቀጥሉት የመግብያ ኮዶች በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፦
1. በ INPS የተሰጠው ፒን;
2. የ SPID ደረጃ 2 ወይም ከዚያ በላይ;
3. የኤሌክትሮኒክ መታወቂያ ካርድ (CIE);
4. የብሔራዊ አገልግሎት ካርድ (CNS).
ፒን ለማግኘት በሚከተሉት መስመሮች መጠየቅ ይቻላል:
- በ www.inps.it ድረገጽ , “Richiesta PIN” በሚለውን የኣገልግሎት መስጫ በመክፈት ;
- በኣረንጓዴ ቁጥር 803 164 (ከቤት ስልክ፡ የነጻ መስመር) ወይም (ከተንቀሳቀሽ ስልክ፡ የነጻ ያልሆነ) 06164164 ደውል.
.

የሪፓርቲ ኢታልያ መለክያዎች

የጣሊያን መንግሥት የአዋጁ ድንጋጌ አፀደቀ፡ በቅርቡ በፓርላማ ውስጥ ውይይት የሚደረግበት ሲሆን ሪፓርቲ ኢታልያ በብዙ መለክያዎች ሕዝቡን ለመቋቋም ቀድሞውኑ ውጤታማ ነው። እዚህ መረጃዎቹን ያንብቡ፦

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ