ለአካለ መጠን ያልደረሱ

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) የድንገተኛ ግዜ ምክንያት መዘጋት ወይም ማቆም የሚያስከትለው ጉዳት ለመቋቋም፡ የጣልያን መንግስት፡ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆችን በሚመለከት ከጸደቁት ደንቦች ጋር የሚዛመዱ ሁሉም ዝርዝሮች ያለማቋረጥ በማደስ በዚህ ገጽ ውስጥ ያቀርባል፡፡

ደህንነታችን በመጠበቅ ወደ ትምህርት ቤት እንመለሳለን

የትምህርት ሻንጣውን ለማዘጋጀት ጊዜው አሁን ደርሷል ፡፡ በዚህ ዓመት ከመጻሕፍትና ከደብተሮች ጋር ወደ አንዳንድ አዳዲስ ልምዶችም መግባት አለብን ፡፡

የተቋሙ ዘመቻ ቁሳቁሶች ለት/ቤት ሰራተኞች ፣ ለቤተሰቦች ፣ ለሴት ተማሪዎችና ተማሪዎች ትምህርትን ዳግም ማስጀመርን ለማጀብ እና አዳዲስ ልምዶች እንዲከበሩ ያበረታታሉ ፡፡

(Fonte: Ministero della Salute)


የሰውነትህን የሙቀት መጠን ለካ
ከመውጣትህ በፊት በየቀኑ ይህንን አድርግ ፡፡ ከ 37.5° በላይ ወይም በኮቪድ - 19 የሚታወቁ ምልክቶች ካለህ በቤትህ በመቆየት ዶክተርህን አነጋግር።

እጅህን ብዙ ግዜ ታጠብ
በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚገኙትን የንጽህና መጠበቅያ ምርቶች ተጠቀም።

ምልክቶቹን ተከተል
መግቢያዎችና መውጫዎች የተለዩ ናቸው ፣ በት/ቤቱ የተዘጋጁትን መመሪያዎች ተከተል።

IMMUNI የሚለውን አፕሊኬሽን ወይም መተግበርያ አውርድ
ዕድሜህ ከ14 ዓመት በላይ ከሆነ አሁን አውርደው፡፡ መተግበሪያው ለኮቪድ - 19 ማንኛውንም ተጋላጭነት ለመለየት ያስችለሃል።.

ርቀትህን ጠብቅ
ማንኛውንም መሰብሰብ አስወግድ። ሁልጊዜ በራስህና በሌሎች መካከል ቢያንስ የአንድ ሜትር ርቀት ጠብቅ።

ጭምብሉን ልበስ
በምትንቀሳቀስበት ግዜ ወይም በጋራ ቦታዎች ውስጥ ሁል ጊዜ ያዘው። በምትቀመጠው የትምህርት ቤት ዴስክ ወይም ጠረጴዛ የአንድ ሜትር ርቀት የሚጠበቅ ከሆነ ማውለቅ ትችላለህ። ከ6 ዓመት በታች ለሆኑ ኣይመለከትም።

በመግቢያዎቹ መረጃ አግኝ
ለአንድ ተማሪ አንድ ረዳት ብቻ ነው የታቀደው። የት/ቤትህ ድረ ገጽ በመግባት ስለ ደንቦቹ ማወቅ ትችላለህ።

እራሳችንን በመጠበቅ እኛም ሌሎችን እንጠብቅ

https://youtu.be/A0YtBBE-Ud4
JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Rientriamo a scuola in sicurezza

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Rientriamo a scuola in sicurezza

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Rientriamo a scuola in sicurezza
JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Rientriamo A Scuola In Sicurezza

18 ዓመት የሞላቸው ወይም በሚቀጥሉት ወራት 18 ዓመት ሊሞላቸው ለተቃረቡ፡ ብቻቸውን ለመጡ ከዕድሜ በታች የውጭ ዜጎች፡ በኣስተዳደሩ ቀጣይነት ላይ ያለው ጠቃሚ መረጃ

ሰላም ለሁላቹህ፡ 

እንደሚታውቁት በድንገተኛው የኮሮና ቫይረስ መስፋፋት፡ የዕለት ተዕለት ኑሮው ብዙ ገጽታዎች ተቀይረዋል። በተለይም ለኣንዳንዶቻቹህ፥ እንደ ትምህርት ቤት፣ የስራ ልምምድ ወይም የመኖርያ ፈቃድ የሚታድስበትና የሚሰጥበት ኣሰራር ላይ ለውጦችና መዘገየት ይታያል።  

በግል ሁኔታዎችህ መረጃ ወይም ማብራርያዎች ከፈለግክ፡ ለሚከተሉትን እርዳታ ጠይቅ፦ 

 • ላንተ ሃላፊነት ለሚወስድ ወይም ቱቶር
 • በምትኖርበት ማዕከል ያሉ ሰራተኞች
 • በማዕከሉ ወይም በፕሮጀክቱ የማትኖር ከሆነ፡ እርዳታ ለሚሰጡ ማሕበራት (ለምሳሌ ኣርቺ)

በኣስተዳደሩ ቀጣይነት ላይ ኣንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎችን እዚህ ላይ ማግኘት ትችላለህ: 

የኣስተዳደሩ ቀጣይነት ምንድነው? 

በጣልያን ሕግ መሰረት የኣስተዳደር ቀጣይነት ማለት፡ ብቻቸውን ለመጡ የውጭ ዜጎችና ከዕድሜ በታች የሚል መኖርያ ፈቃድ ላገኙ ወጣቶች፡ ዕድሜያቸው 18 ሊደርስ ለተቃረቡ ሁሉ፡ በሚኖሩበት ማዕከልና ከጣልያኑ ህብረተሰብ የጀመሩት መቀላቀል ቀጣይነት ኢንዲኖረውና፡ እስከ 21 ዓመት ዕድሜያቸው ድረስ በማዕከሉ ያላቸው ቆይታ እንዲራዘምላቸው እድል የሚሰጥ ማለት ነው።. 

የኣስተዳደሩ ቀጣይነት የሚመለከተው ለማነው? 

የኣስተዳደሩ ቀጣይነት ለሁሉም ብቻቸውን ለመጡ ከዕድሜ በታች ለሆኑና 18 ዓመት ዕድሜያቸው ሊሞላ ለተቃረበ፡ ከዕድሜ በታች የሚለውን መኖርያ ፈቃድ ላገኙ የውጭ ዜጎች ነው። 

ለኣስተዳደሩ ቀጣይነት ማመልከቻ የሚያቀርበው ማነው?  

 • ሃላፊነት የወሰደልህ ወይም ቱቶርህ

ወይም 

 • የማዛገጃ ቤቱ ማህበራዊ ኣገልግሎት፡ ከምትኖርበት ማዕከል ባሉ ሰራተኞች ኣማካኝነትድጋፍ በማግኘት

  ማስታወሻ፦ይህንን ጥያቄ በቱቶሩ ወይም በማዛገጃ ቤቱ ማህበራዊ ኣገልግሎት በኩል ለማስገባት ችግር ካጋጠመህ ወደምትፈልገው እርዳታ የሚሰጥ ማሕበር በመሄድ (ለምሳሌ ኣርቺ) ወደሚመለከተው ፍርድ ቤት እንድታመለክት ይረዱሃል። 

ለኣስተዳደራዊ ቀጣይነት እንዴት ማመልከት ይቻላል? 

የኣስተዳደሩ ቀጣይነት ማመልከት የሚቻለው: ከዕድሜ በታች ለሆኑ የሚከታተለውን ፍርድ ቤት በማመልከት ነው። ( ማመልከቻ የሚቀርቡበት ሰነዶች በኢንተኔት ገብተህ ማግኘት ትችላለህ)  

የኣስተዳደሩ ቀጣይነት ማመልከቻ፡ ማህበራዊ ኣገልግሎቶቹ በማዕከሉ ቀጣይነት እንድታገኝና ከመጣህበት ጀምሮ ከህብረተሰቡ የጀመርከውን ውህደት እንዲቀጥልና እስከ 21 ዓመት ዕድሜህ እንዲራዘምልህ ለፍርድቤቱ ጥያቄ ያቀርባሉ። 

የኣስተዳደሩ ቀጣይነት ማመልከቻ የት መቅረብ ኣለበት? 

 • ለፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ሕግ 

ወይም 

 • ለፍርድ ቤቱ

የኣስተዳደሩ ቀጣይነት ማመልከቻ መቼ መቅረብ ኣለበት? 

18 ዓመት ከመድረስህ በፊት 

ምን ዓይነት መልስ ይሰጡኛል? 

ፍርድ ቤቱ የግል ታሪክ ሰነድህን ከመረመረ ቦኃላ፡ ለማሕበራዊ ኣገልግሎት ሰጪዎች ኣደራ መስጠቱን ላይ መወሰን ይችላል። ስለዚህ በማዕከሉ 21 ዓመት እስኪሞላህ እንድትኖር ይራዘምልሃል።. 

ኣሉታዊ መልስ ከተገኘስ? 

ይህ ስያጋጥምህ ወደ ማዕከሉ ሰራተኞች ወይም ኣንተን የሚከታተል ቱቶር በመሄድ: ስለ ሁኔታው ኣጥጋቢ መረጃ እንዲሰጡህ እንድትጠይቅ ይመከራል። 

በዚህ የድንገተኛ ኣደጋ ግዜ ውስጥ የኣስተዳደራዊ ቀጣይነት ማመልከቻ ማቅረብ ይቻላል? 

ኣዎ፡ ሙሉ መረጃ ለማግኘት ለቱቶርህ ወይም ለምትኖርበት ማዕከል ሰራተኞች ስለ ሁኔታው ሙሉ መረጃ እንድትጠቅ ይመከራል። 

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Prosieguo Amministrativo

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Prosieguo Amministrativo

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Prosieguo Amministrativo

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Prosieguo Amministrativo

ከቤተሰብህ ለመቀላቀል የምትጠብቅ ከዕድሜ በታች የምትገኝ ታዳጊ ነህ?

ሰላም!

“ደብሊ III” ባዘጋጀው የኣሰራር ደንብ ከቤተሰቦችህ ኣባል ጋር ለመገናኘት እየጠበቅክ ከሆነ፡ የሚከተሉትን መረጃዎች በጥንቃቄ ኣንብብ።

 • እንደምታውቀው ከ ኮቪድ - 19 የጤናው ድንገተኛ አደጋ ጊዜ ሁሉንም የአውሮፓ ህብረት አገሮችን ይመለከታል ፡፡ የሁሉም መንግስታት ዋና ዓላማ የሰዎችን ጤና መጠበቅ ነው። ይህ በአሁኑ ጊዜ የሚከናወነው በአገሮች ውስጥ እና በውጭ የሚገኙትን ጉዞ በመቀነስ ብቻ ነው ፡፡
 • በአሁኑ ሰዓት በኣሰራሩ ሂደት መጀመርያ ላይ ከሆንክ ኣንተና ኣውሮጳ ውስጥ ከሚገኘው በተሰብህ የሚመለከቱን ሰነዶች ለማፈላለግ ግዜውን ተጠቀምበት። ከተቻለ ፡ ፎቶግራፍ፣ የልደት የምስክር ሰርተፊኬት፣ መታወቅያ ወረቀት ወይም ዝምድናቹህን የሚያመለክት ማንኛውም ማስረጃ እንዲሊክልህ ቤተሰብህን ኣነጋግር።
 • ከድንገተኛ አደጋው ጋር የሚወሰዱት እርምጃዎች የመቀላቀልህ ሂደት ቢዘገዩም እንኳን የመሄድህን ጉዳይ አያግዱትም፡ እያጋጠመን ያለው ድንገተኛ ጊዜያዊ ነው: ለዘላለም አይቆይም፦ አትጨነቅ፣ ብቻ ታጋሽ መሆን ኣለብህ።
 • የቤተሰብ መልሶ መገናኘት ካመለከትክና 18 ዓመት ሊሞላህ ከሆነ፡ ወይም ካመለከት ቦኃላ ወድያው ከሞላህ ኣትጨነቅ። ምንም እንኳን 18 ዓመት ቢያልፍህም ያመለከትከውን ግን ሂደቱ ይቀጥላል።
 • ዕድሜህ 18 ዓመት ሊደርስ ከተቃረበና ከኣውሮጳ ህብረት ካለው ቤተሰብህ ለመቀላቀል ከፈለግክ፡ ግን በቤተሰብ መልሶ ማገናኛ ገና ካላመለከትክ፡ ወድያውኑ ያንተ ሃላፊነት ለወሰደው ፣ ለኦፕሬተርህ ፣ ለህግ አማካሪህ ፣ ለማህበራዊ ሰራተኛች ኣነጋግር። ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉና ሊረዱህ ይችላሉ።
 • ጥርጣሬ ካለህ ስለዚህ ጉዳይ ተናገር፦ ኦፕሬተሩ ፣ ያንተ ሃላፊነት ለወሰደው ፣ የሕግ አማካሪው ኣንተንና ቤተሰብህ የሚደግፉ እዚህ አሉ እንዲሁም ጠቃሚ መረጃ ሊሰጡህ ይችላል ፡፡

ኣስታውስ፡ የዱብሊን ሕግ ወደ ቤተሰቦችህ ለማድረስ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ህጋዊ መንገድ ነውና ተረጋጋ።

ስለ መልሶ ማገናኘት ጥያቄዎች ካለህ የ EFRIS ፕሮጀክት መልስ ሊሰጥህ ይችላል፡ ደውልልን ፣ ጻፍልን ወይም ኦፐሬተርህ በ ኢ-መይል ኣድራሻችን እንዲያግኘን ጠይቅ። ኢ-መይል ኣድራሻችን፦ progettoefris@cidas.coop ወይም በስልክ ቁጥራችን +39 3404277780; +39 3428735259 ደውል።

የበለጠ መረጃ ከፈለግክ የጁማ ማፕ ድርጣቢያ https://coronavirus.jumamap.com/it_it/ ተመልከት፡ ወይም ለኑሜሮ ቬርደ ኦፐሬተሮች በ 800905570/3511376355 ደውል ወይም ኢ-መይል numeroverderifugiati@arci.it ጻፍልን።

(Thanks to CIDAS)

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Sei un minore in attesa di ricongiungimento?

Ricongiungimento familiare

በደብሊን III ደንብ መሠረት ብቻቸው ለተሰደዱ ከዕድሜ በታች የሆኑ የውጭ ዘጎች፡ የቤተሰብ መልሶ ማገናኘት ኣሰራር በድንገተኛው ኮቪድ 19 ግዜ

ከዕድሜ በታች ለሆኑ የውጭ ዜጎች የቤተሰብ መልሶ ማገናኛ ኣሰራር ፡ በደብሊን III ኣንቀጽ 8 መሰረትና፡ ኣሁን ባለው ግዝያዊ የጤንነት ችግር ፡ ኮቪድ 19 በተመለከተ - ጥሩ የኣሰራር ልምዶች

ታዳጊው በየትኛው ደረጃ የኣሰራር ሂደት ይገኛል?

 1. ታዳጊው በሌላ የኣውሮጳ ህብረት ከሚገኝ ቤተሰቡ ለመሰባሰብ ፍላጎት እንዳለው ኣሳይቶ ነበር፡ ግን ለዓለም ኣቀፍ የጥገኝነት ጥያቄ ገና ኣሻራ ኣላደረገም፧

በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ስብሰባ 0020359 ከ 9 ማርች 2020 ባጸደቀው መሰረት፡ የኢሚግረሽን ጽሕፈት ቤት ስራውን እየቀጠለ ነው፡ ሁሉም ሳይሆን፡ ሞዴል ሲ-3 ሞልቶ ለማቅረብና የደብሊን ኣሰራሩን እንደቀጠለ ነው። ስለሆነም፧ ታዳጊው በቅርቡ ለኣካለመጠን የሚደርስ ካልሆነ በስተቀር፡ የዓለም ኣቀፍ ጥበቃ ጥያቄና ለኣሻራ፡ የኢሚግረሽኑ የኣሰራር ሁኔታ መጠበቅ ኣለበት። በሚጠብቅበት ግዜም ኣሰፈላጊ ሰነዶችን እንዲያዘጋጅ ይመከራል። እነሱም፡ (በታዳጊውና በቤተሰቡ ያለው የዝምድና ዓይነት፣ የታዳጊው ፍላጎትና የቤተሰቡ የፍላጎት ስምምነት፣ ታዳጊው ስለቤተሰቡና ስለ ራሱ ለሚይደርገው ቃለ መጠይቅ፣ የታዳጊውና የቤተሰቡ መታወቅያ)።

 1. ታዳጊው የዓለም ኣቀፍ ጥበቃ ጥያቄው ኣቅርቦ ኣሻራ ከተወሰደለት ቦኃላ የ ሲ-3 ሰንድ ግን ኣሁን ባለው የኢሚግረሽን ኣሰራር ሞምላት ኣልቻለም፧:

ኣሻራ ከተወሰደ ቦኃላ የ 3 ወር ግዜ ኣለ። በዚህ 3 ወር ውስጥ፡ በደብሊኑ ህግ መሰረት የቤተሰብን መልሶ ማገናኘት ኣሰራር ማመልከት ይቻላል። የማብቅያው ግዜ ኣልተቀየረም። ለምሳሌ የማብቅያ ግዜው በኤፕሪልና በግማሽ መይ ከሆነ፡ የጥያቄው ሰነድ በቀጥታ ወደ ደብሊን በመስመር ወይም በቴሌማቲክ እንዲላክ ይመከራል። በዚህ ረገድ፡ የኢሚግረሽን ጽሕፈት ቤት ስራውን በሚጀምርበት ግዜ፡ የ ሲ-3 ሞደሉን ማስፈጸም ኣስፈላጊ ነው።

 1. የቤተሰብ መልሶ ማገናኘት ፕሮግራም በተሳካ ተጠናቆ፡ በኣንዳንድ የኢሚግረሽኑ ኣሰራር መቆም፡ የመልሱ ውጤት ኣልተሰጠም፧:

የሚመለከተው የኢሚግሬሽን ጽሕፈት ቤት ውጤቱ በፔክ ወይም ከሌሎቹ ጽሕፈት ቤቶች በሚያመች ቢላክ ይመረጣል። (ለምሳሌ፡ በኣደራ ደብዳቤ)።የመሄጃ ሰነዱ (ኑላ ኦስታ) ከተዘጋጀ ቦኃላ ሰነዱ ወደ ሚመለከተው የፍርድ ቤት ዳኛ መላክ ይቻላል።

 1. የቤተሰብ መልሶ ማገናኘት ፕሮግራሙ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ፡ በድንገተኛው የኮቪድ 19 እቀባዎች ምክንያት መሄድ ኣልተቻለም፧

ለግዜው ከጣልያን ወደ ሌላ የኣውሮጳ ሕብረት ኣገራት መሄድ ቆመዋል። በደብሊን III በኣንቀስጽ 29 ባስቀመጠው ሕግ መሰረት፡ መሄድ ከተፈቀደለት ቀን ጀምሮ በስድስት ወራት ውስጥ ወደ ተፈቀደለት ኣገር መግባት ኣለበት። የመውደቅያው ግዜ ከተቃረበ፡ እርዳታ ለማግኘት በፍጥነት ወደ ደብሊኑ ጽሕፈት ቤት መገናኘት ኣለበት።

N.B. በዳብሊን III ደንብ መሠረት እንደገና የመሰባሰብ ሂደት ከመደምደሙ በፊት ታዳጊው 18 ዓመት ቢሞላው የኣሰራሩ ሂደት ኣያደናቅፍም። የኣሰራሩ ውጤት ታዳጊው 18 ዓመት ከመድረሱ በፊት ባመለከተው መሰረት ነው የሚከናወነው።

የቀረቡት መግለጫዎች ሙሉ በሙሉ ኣጥጋቢ ኣይደሉም። የታዳጊዎች የቤተሰብ መልሶ ማገናኘት ኣሰራር: በእያንዳንዱ ኣሰራር፡ የራሱ ውጤት ኣለው።

በተለይ በቁጥር 1 እና 2 በተገለጹት ሁኔታዎች የምትገኝ ከሆነ፡ እያንዳንዱ እንቅፋት የሚሆንህን ጉዳይ ማሳወቅ በጣም ጠቃሚ ነው።

የ EFRIS ፕሮጀክት ቡድን ግንኙነቱን ወደ ዱብሊን ክፍሉ ያስተላልፋል፡ በዚህም: በኢሚግረሽን የሞደል ሲ-3 ምዝገባና የጉዳዩ የመውደቅያ ግዜን ይከታተላል። የ EFRIS ፕሮጀክት ቡድን ከዕድሜ በታች ለሆኑ ታዳጊዎች፡ የቤተሰብ መልሶ ማገናኘት ጉዳዮችን ለመደገፍ ይሰራል። ለማንኛውም ጥርጣሬ ካለህ ወይም ማብራሪያ ለማግኘት ፦

ኢ-መይል progettoefris@cidas.coop;

ስልክ ቁ. +39 3404277780; +39 3428735259 በኣጠቃላይ ኮቭድ- 19 በጥገኝነት ፈላጊዎችና ጥገኝነት ባገኙ ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ፡ መረጃ፣ ኣስፈላጊ ነገሮችና በየግዜው እየታደሱ ለሚወጡ መረጃዎች ለማግኘት የጁማ ማፕ ድረገጽ በመግባት ተከታተሉ። https://coronavirus.jumamap.com/it_it/ ወይም የኣርቺ (ARCI) ኦፐሬተሮች፡ በኑሜሮ ቨርደ 800905570/3511376355 በመደወል ወይም በኢ-መይል numeroverderifugiati@arci.it መጻፍ ትችላላቹህ።

ሰነዶች

የቪዲዮ

MAPPA

MINIILA APP: una mano tesa per ogni minore che arriva  in Europa,  per consentirgli di arrivare in un luogo sicuro e per essere trattato con amore, rispetto e dignità.

Cerchi informazioni o aiuto nel paese in cui ti trovi? Scarica l’applicazione qui

ፖድካስት

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ