ህጎች እና ባህሪዎች

የጣልያን መንግስት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል፡ ሕብረተሰቡን መከታተል ያለበትን የተለያዩ ጥብቅ መለክያዎች ኣውጥተዋል። መከተል ያለብንን ሁልንም መለክያዎች በየግዜው በማስተካከል በዚህ ክፍል ያቀርባል።

በመላው ብሔራዊ ክልል ውስጥ ኢንፌክሽኑን እንዳይዛመት ለመቆጣጠር አስቸኳይ እርምጃዎች - እስከ ኖቨምበር (ህዳር) 13 ቀን 2020 ድረስ የሚሰራ

የጭምብሎች ኣስገዳጅ ኣጠቃቀም

ጭምብሎች መለበስ ያለባቸው፥

 • በሁሉም ክፍት ቦታዎች
 • ጭምብሉ በክፍትም ይሁን በዝግ ቦታዎች ግዴታ ነው፡ ከቤትዎ በስተቀር 

ጭምብሉን መጠቀም ለሚከተሉትን ግዴታ አይደለም፥

 • ከስድስት ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች
 • ጭምብልን ከመጠቀም የማይስማማ በሽታ ላላቸው ሰዎች ወይም የአካል ጉዳተኞች
 • የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በሚከናወንበት
 • የሚከተሉትን ልዩነቶች መሰረት በማድረግ፡ ከሌሎቹ ሰዎች ቢያንስ አንድ ሜትር የደህንነት ርቀትን መጠበቅ ሁልጊዜ ግዴታ ነው ፡፡

የማህበረሰብ ጭምብሎች ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ፤ ማለትም የሚጣሉ ጭምብሎች ወይም የሚታጠቡ ጭምብሎች ፣ እራስዎንም የሚያመርቱ ቢሆንም ፣ በቂ መከላከያ ለመስጠት ተስማሚ እስከሆኑ ድረስ ፡፡

ስፖርትና አካላዊ እንቅስቃሴ

✓ የአካል እንቅስቃሴን በሚመለከት (ለምሳሌ በፍጥነት መራመድ) ብያንስ የ1 ሜትር ርቀት በመጠበቅ ማካሄድ ይፈቀዳል።

✓ ቢያንስ 2 ሜትር ርቀትን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን (ለምሳሌ መሮጥ) ማከናወን ይፈቀዳል

✓ ስፖርቶችና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች በጂሞች ፣ በመዋኛዎች ፣ በስፖርት ማዕከሎችና ክለቦች (የህዝብና የግል) ሕጎችን እስከተከበሩ ድረስ፡ ማህበራዊ ርቀቶችን በመጠበቅና መሰባሰብን በማስወገድና ማከናወን ይፈቀዳሉ ፡፡

✘ አማተር ስፖርት፡ ከአማተር ስፖርት ጋር የተያያዙ ሁሉም ውድድሮችና፡ የአማተር እንቅስቃሴዎች የሚከተሉ የተከለከሉ ናቸው፡፡

✓ እውቅና ከተሰጣቸው የስፖርት ማሕበራት፣ በጣልያን ብሔራዊ ኮሚቴ፣ በጣልያን ፓራሊምፒክ እውቅና ከተሰጣቸውና ስርአቱን በተከተሉ የስፖርት ማሕበራትና ስፖርት የሚያስተዋውቁ ማሕበራት የመተላለፍ ኣደጋውን በመከላከልና በመቀነስ፡ ስፖርቱን ለማከናወን ይፈቀዳል።

✓ የስፖርት ውድድሮች (ለምሳሌ በስታዲየም)፡ ከሚይዘው መጠን እስከ 15% የሚሆነውን ተመልካች መኖር ይፈቀዳል እናም በክፍት ቦታ በማንኛውም ሁኔታ ከ 1000 በላይ ተመልካቾችና በዝግ ከ 200 አይበልጡም ፡፡ የአንድ ሜትር ርቀት ማስጠበቅና በመግቢያው የትኩሳት መጠን መለካት አለበት።

ዝግጅቶች ፣ ትያትሮች ፣ ሲኒማ ቤቶች ፣ የጭፈራ ቦታዎች

✓ ሲኒማ ቤቶች ፣ ቲያትሮችና ኮንሰርቶች ቢያንስ 1 ሜትር የደህንነት ርቀቱ በማክበር የሚቻል ሲሆን ቢበዛ 1000 ተመልካቾች በክፍት ትርኢቶችና በዝግ ትርኢቶች 200 ተመልካቾች እንዲኖሩ ተደርጓል ፡፡.

✘ በዳንስ ቤቶች ሆነ በጭፈራ ቤቶች የሚከናወኑ ዝግጅቶች ተከልክለዋል።

✓ማሕበራዊ ርቀቶችና የወጣውን ሕግ በማስከበረ ባዛሮችና ስብሰባዎች ማድረግ ይፈቀዳል።

✓ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች፡ የስታቲክሱ መርህ በመከተል ማሕበርዊ ርቀቶች በማክበርና የተደነገገውን ሕግ በመከተል መደረግ ይቻላል።

የግል ድግሶች - በቤት ውስጥ ወይም ከቤት ውጭ

✘ የግል ድግሶች ከቤት ውስጥም ሆነ ከቤት ውጭ የተከለከሉ ናቸው። በቤትዎ ውስጥ አብረው የማይኖሩ ከ 6 የማይበልጡ ሰዎችን ለመቀበል በጥብቅ ይመከራል ፡፡

ምግብ ቤቶች ፣ ቡና ቤቶች ፣ መጠጥ ቤቶች ፣ የኬክና የአይስክሬም ሱቆች
 • የኣቅርቦቱ ፍጆታ በጠረጴዛ ቁጭ ብለው ለሚስተናገዱ እስክ 24:00 ሰዓት (እኩለ ለሊት) ክፍት ሲሆን ቁጭ ብለው ለማይስተናገዱ ደግሞ እስከ 21:00 ሰዓት ይፈቀዳል።

✓ ወቅታዊ ደንቦችን በማክበር በታዘዙት መሰረት ምግብ በየቤቱ ማድረስ ይፈቀድላቸዋል።

ትምህርት ቤቶች

✘ በትምህርት ቤት የሚዘጋጁ ጉዞዎች የተከለከሉ ናቸው።

የጭምብሎች ኣስገዳጅ ኣጠቃቀም

የ 7 ጥቅምት (ኦክቶቨር) የሕግ ድንጋጌ ሁልጊዜ የመተንፈሻ መከላከያ ጭንብሎች ከእርስዎ ጋር የመያዝ ግዴታን ያመለክታል። ጭምብሎች መለበስ ያለባቸው፥

 • በሁሉም ክፍት ቦታዎች
 • ጭምብሉ በክፍትም ይሁን በዝግ ቦታዎች ግዴታ ነው፡ ከቤትዎ በስተቀር 

ጭምብሉን መጠቀም ለሚከተሉትን ግዴታ አይደለም፥

 • ከስድስት ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች
 • ጭምብልን ከመጠቀም የማይስማማ በሽታ ላላቸው ሰዎች ወይም የአካል ጉዳተኞች
 • የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በሚከናወንበት

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Utilizzo obbligatorio delle mascherine

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Utilizzo obbligatorio delle mascherine

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Utilizzo obbligatorio delle mascherine

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Utilizzo obbligatorio delle mascherine

ደህንነታችን በመጠበቅ ወደ ትምህርት ቤት እንመለሳለን

የትምህርት ሻንጣውን ለማዘጋጀት ጊዜው አሁን ደርሷል ፡፡ በዚህ ዓመት ከመጻሕፍትና ከደብተሮች ጋር ወደ አንዳንድ አዳዲስ ልምዶችም መግባት አለብን ፡፡

የተቋሙ ዘመቻ ቁሳቁሶች ለት/ቤት ሰራተኞች ፣ ለቤተሰቦች ፣ ለሴት ተማሪዎችና ተማሪዎች ትምህርትን ዳግም ማስጀመርን ለማጀብ እና አዳዲስ ልምዶች እንዲከበሩ ያበረታታሉ ፡፡

(Fonte: Ministero della Salute)


የሰውነትህን የሙቀት መጠን ለካ
ከመውጣትህ በፊት በየቀኑ ይህንን አድርግ ፡፡ ከ 37.5° በላይ ወይም በኮቪድ - 19 የሚታወቁ ምልክቶች ካለህ በቤትህ በመቆየት ዶክተርህን አነጋግር።

እጅህን ብዙ ግዜ ታጠብ
በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚገኙትን የንጽህና መጠበቅያ ምርቶች ተጠቀም።

ምልክቶቹን ተከተል
መግቢያዎችና መውጫዎች የተለዩ ናቸው ፣ በት/ቤቱ የተዘጋጁትን መመሪያዎች ተከተል።

IMMUNI የሚለውን አፕሊኬሽን ወይም መተግበርያ አውርድ
ዕድሜህ ከ14 ዓመት በላይ ከሆነ አሁን አውርደው፡፡ መተግበሪያው ለኮቪድ - 19 ማንኛውንም ተጋላጭነት ለመለየት ያስችለሃል።.

ርቀትህን ጠብቅ
ማንኛውንም መሰብሰብ አስወግድ። ሁልጊዜ በራስህና በሌሎች መካከል ቢያንስ የአንድ ሜትር ርቀት ጠብቅ።

ጭምብሉን ልበስ
በምትንቀሳቀስበት ግዜ ወይም በጋራ ቦታዎች ውስጥ ሁል ጊዜ ያዘው። በምትቀመጠው የትምህርት ቤት ዴስክ ወይም ጠረጴዛ የአንድ ሜትር ርቀት የሚጠበቅ ከሆነ ማውለቅ ትችላለህ። ከ6 ዓመት በታች ለሆኑ ኣይመለከትም።

በመግቢያዎቹ መረጃ አግኝ
ለአንድ ተማሪ አንድ ረዳት ብቻ ነው የታቀደው። የት/ቤትህ ድረ ገጽ በመግባት ስለ ደንቦቹ ማወቅ ትችላለህ።

እራሳችንን በመጠበቅ እኛም ሌሎችን እንጠብቅ

https://youtu.be/A0YtBBE-Ud4
JumaMap – COVID-19 in Italy · [PIDGIN ENGLISH] Rientriamo a scuola in sicurezza

JumaMap – COVID-19 in Italy · [SONINKE] Rientriamo a scuola in sicurezza

JumaMap – COVID-19 in Italy · [PULAR] Rientriamo a scuola in sicurezza
JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Rientriamo A Scuola In Sicurezza

ከሜይ 18 ጀምሮ ለመጓዝ በሚመለከት የወጡ አዳዲስ ህጎች

በአጠቃላይ ከግንቦት 18 ጀምሮ ባለህበት ክልል ውስጥ ያለ ገደብ መሄድ ትችላለህ፡፡ ሆኖም ባለሥልጣኖቹ የኮቪድ - 19 ስርጭትን ለመግታት ወደ አንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች መጓዝ ሊገድቡ ይችላሉ።.

ከአንድ ክልል ወደ ሌላው የሚደረግ ጉዞ አሁንም ውስን ነው ፡፡ በአጠቃላይ በምትኖርበት ክልል ውስጥ መቆየት አለብህ፡፡ ወደ ሌላ ክልል ለመዘዋወር ብቸኛና ትክክለኛ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦ በስራ ምክንያት ከነማስረጃው በማቅረብ፣ በኣስቸኳይ ጉዳይ ምክንያት፣ በጤና ምክንያት ወይም ወደ ቤት ፡ ወደ መኖርያ ሰፈር ለመመለስ ነው።

በአጠቃላይ ከጁን 3 - ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል ያለገደብ ለመንቀሳቀስም ይቻላል ፡፡ ሆኖም ባለሥልጣኖቹ የኮቪድ - 19 ስርጭትን ለመገደብ ወደ አንዳንድ የጣልያን አካባቢዎች መጓዝ ሊገድቡ ይችላሉ።

ኣሁንም ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ወይም በክፍት ቦታዎች መሰባሰብ ክልክል ነው። ለማንኛውም ወደምትፈልግበት ቦታ ለመሄድ ምን ማድረግ እንዳለብህ ኣዳዲስ መረጃዎች ለማግኘት፡ ክልልህን እያዘመነ የሚያወጣውን መረጃ በድረገጹ ተመልከት።.


የኮቪድ-19 ኣዲስ ሕጎችና ገደቦች ፡ ከ 4 እስከ 18 ሜይ 2020

በኤፕሪል 26-2020 የወጣው ኣዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትር ውሳኔ፡ ከ 4 ሜይ እስከ 18 ሜይ 2020 በስራ ላይ የሚውለው ለድንገተኛው የኮሮና ቫይረስ የነበረው ሕግ በመቀየርና ኣዲሱን ኣጠቃቀም በተግባር የሚያውል ስራ ይጀምራል።

ኣሁንም የግድ በኣካል መራራቅ ኣለብን?

ጭምብሎችና ጓንቶች ወይም ሌሎች መከላከያ መሳርያዎችን በመጠቀምና ቢያንስ የኣንድ ሜትር የኣካላዊ ርቀት መጠበቅ ግዴታ ሆኖ ይቆያል። ህዝብ የሚጠቀምባቸው ዝግ ቦታዎች ጭምብሎች መጠቀም ግዴታ ነው፡ በህዝብ ማጓጓዣዎችም ጭምር።.

ጉዞ ይፈቀዳል?

በኣንድ ክልል ውስጥ መጓዝ ይፈቀዳል፦ ለስራ፣ ለጤንነትን ለኣስፈላጊ ጉዳዮች እንዲሁም ቤተሰብ ለመጠየቅም ጭምር፡ ግን የኣንድ ሜትር የሰዎች መርራቅ በማክበርና ጭምብሎችን በመጠቀም ሲሆን መሰባሰብ ግን ሕጉን ኣይፈቀድም። ከክልል ውጭ መንቀሳቀስ የሚፈቀደው፡ ለስራ፣ ለጤንነት፣ ለኣስቸኳይ ጉዳይ ምክንያቶች ብቻ ነው። ወደ ቤት ወይም ወደ መኖርያ ቦታ መመለስ ይቻላል።

ለበለጠ መረጃ፡ ለድንገተኛ ኣደጋ ኮቪድ-19 ለተዘጋጀው የክልሉ ኑሜሮ ቬርደ ማነጋገርን ይመከራል። እንዲሁም ለሌሎች ኣስፈላጊ ጉዳዮች ወደ ክልልዎ ሲመለሱ፣ ለኳራንቴና እና ራስዎን ለማግለል ጭምር።

ኣዲሶቹ በራስ የሚዘጋጁ ማረጋገጫዎች የትኞቹ ናቸው?

በራስ የሚዘጋጅ የመንቀሳቀሻ ሰነድ

ወደ ጣልያን ለመግባት በራስ የሚዘጋጅ የማረጋገጫ ሰነድ

 

ወደ ፓርክ መሄድ እችላለሁ?

የልጆች የመወጫቻ ስፍራዎች በመዝጋትና ቢያንስ የኣንድ ሜትር ርቀት በማክበር ወደ መናፈሻዎች፣ የኣትክልት ስፍራዎችና የህዝብ መዝናኛ ቪላዎች መሄድ ይቻላል። የደህንነቱ ደንቦች ለማስከበር ካልተቻለ፡ ከንቲባዎቹ ወደ መናፈሻዎች የመግባት ሁኔታን መገምገም ይችላሉ።

ስፖርትና የኣካል እንቅስቃሴዎችን ማከናወን እችላለሁኝ? ከዕድሜ በታች የሆነ ከኔ ጋር መሄድ ይችላል?

በተናጠል ማከናወን ይቻላል። ለኣካለ መጠን ላልደረሱ ልጆችና በራሳቸው ለመንቀሳቀስ ሙሉ ኣቅም ከሌላቸው ሰዎች ጋር በመሄድ ስፖርት ወይም የኣካል ብቃት እንቅስቃሴ ማከናወን የሚቻል ሆኖ፡ ለስፖርት ቢያንስ የሁለት ሜትር ርቀት ለሌሎች እንቅስቃሴዎች ደግሞ የኣንድ ሜትር ርቀት በመጠበቅ።

የቀብር ስነስርዓቶችና ሃይማኖታዊ ስነስርዓቶችን ማከናወን ይፈቀዳሉ?

የሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶችን በተመለከተ ቤተሰቡና የቅርብ ዘመዶች ለሚከበረው የቀብር ስነ ስርዓት መካፈል ይችላሉ፡ በክፍት ቦታ የሚዘጋጅ ከሆነ የሚመረጥ ሆኖ ጭምብሎችን በመጠቀምና የሰዎችን መርራቅ በመጠበቅ እስከ 15 ሰዎች መካፈል ይችላሉ።

ወደ ምግብ ቤት ወይም ወደ ፈጣን ምግብ ኣዘጋጆች መሄድ እችላለሁ?

አዎ ፡ ግን የታዘዙ ምግቦች ለመውሰድ ብቻ ነው። ለዚህም ምግብ ቤቶች የታዘዙ ምግቦች ለማድረስ ወይም ኣዘው ለሚወስዱ ሰዎች ክፍት ነው፡ የሰዎች መርራቅ እንደተጠበቀ ሆኖ፡ በምግብ ቤቱ ውስጥ መብላት ኣይቻልም። 

ትኩሳት ካለብኝ ምን ማድረግ አለብኝ?

ከ 37.5 ዲግሪ በላይ ትኩሳት ያለውና በመተንፈሻ ኣካላት ሕመም የሚሰማው ሰው፡ መጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን እቤት ውስጥ መቆየትና ሓኪሙን የማሳወቅ ግዴታ ኣለበት።

በሓኪም የታዘዘ መድሓኒት በኢ-መይል ወይም በሞባይል ስልክ መልእክት መቀበል ይቻላል?

ኣዎ፡በ19ማርች 2020 በወጣው ትእዛዝ መሰረት በሓኪም የሚላከው የኤለክትሮኒክ ኮድ ቁጥር በመጠቀም፡ ወረቀቱን በኣካል ከሓኪሙ መሳብ ኣያስፈልግም። ፋርማሲስቱ ኣንዴ የኤሌክትሮኒኩ ኮድ ቁጥርና የሕክምና መታወቅያ ኮድ (ኮዲቸ ፊስካለ) ካገኘ ቦኃላ የሚፈለገውን መድሃኒት ይሰጣል።.

በብሔራዊው የመገደብ እርምጃዎች ምክንያት ለሴቶች የጸረ ጥቃት ኣገልግሎት የሚሰጡ ማእከላት እንቅስቃሴኣቸውን ኣቁመዋል?

ኣላቆሙም፥ በሁከት የተጠመዱና በቁጡ መንፈስ እየተከታተሉ ከሚያስቸግርዋቸው፡ ሴቶች ብቸኝነት ሊሰማቸው ኣይገባም። ለ 24 ሰዓታት ኣገልግሎት ከሚሰጠውን ማእከል በነጻ ቁጥር 1522 በመደወል እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪ በጥቃት ክስተቱ ሴቶቹን ወደ ማእከሉ ለመሄድ ኣስፈላጊ በሚሆንበት ግዜ፡ መንቀሳቀስ እንደሚፈቀድላቸው በ 11 ማርች የወጣው ህግ ይጠቅሳል።

በአሁኑ ጊዜ ከ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተዛመደ ጭንቀት ውስጥ ላሉ ሰዎች የስነልቦና ድጋፍ ለማድረግ ተነሳሽነት አለ

በጤናና በሲቪል ጥበቃ ሚኒስቴር የሚተገበሩ የስነ ልቦና እርዳታ፡ የኑሜሮ ቨርደ ነጻ መደወያ ቁጥር 800.833.833 ከኤፕሪል 27 ጀምሮ ስራ ላይ ውለዋል። ከጣልያን ውጭም በ 02.20228733 መደወል ይቻላል። ሁልግዜ ከ 08:00 – 24:00 ድረስ በየቀኑ ይሰራል። መስማት የሚሳናቸውም መጠቀም የሚችሉበት የኣሰራር ሂደት ኣላቸው።

የበለጠ ለመረዳት ጤና ሚኒስቴር ለኣዲሱ ኮሮና ቫይረስ የስነልቦና ድጋፍ የኑሜሮ ቨርደ ድረገጽ ተመልከቱ። Numero verde di supporto psicologico .

JumaMap – COVID-19 in Italy · [BAMBARA] Nuove regole e limitazioni – dal 4 al 18 maggio 2020

ትኩረት፦ ከውጭ ሃገር የሚመለሱ ጣልያንያውያን እና የውጭ ዜጎች በጣልያን

ለማውረድ እዚህ ይጫኑ:

1. በጣሊያን ውስጥ ለመንቀሳቀስ በራስ የሚዘጋጅ የመንቀሳቀሻ ሰነድ፡ ኣዲስ ሞዴል 26.03.2020 NUOVO MODELLO 26.03.2020

2. በራስ የሚዘጋጅ የመንቀሳቀሻ ሰርተፊኬት ወይም ሰነድ፡ ሞዴል MODELLO

 • ከ 12 ማርች ቦኃላ፡ ከውጭ ወደ ጣልያን ለመግባት የሚያገለግሉ ህጎች የትኞቹ ናቸው?
 1. የትራንስፖርቱ ማመላለሻም ሃላፊነት ይወስዳል፡ በራስ የሚሞላው የጉዞ ምክንያት ሰነድ (የሞዴሉ ሊንክ)፡ በመውጫ ሰዓት ሞልቶ የሚተወው የጉዞው ምክንያት በደንብ መግለጽ ኣለበት በ (ጤና፣ ስራ፣ ኣስፈላጊ ጉዳዮች)። ለ 14 ቀናት ተወሽቦ የሚቆዩበት ቦታም ማሳወቅ። መዳረሻው እንደደረሱ የሚጠቀሙት ማጓጓዣ ወይም የራስ ማጓጓዣ የሚጠቀሙ ከሆነ፡ የሚገኙበት ስልክ ቁጥር የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር ጭምር ማሳወቅ። የጉዞው ምክንያት ኣስፈላጊ በመሆኑ፡ በድረግጻችን ካሰፈርናቸው ምክንያቶች ይመልከቱ።link al modulo 
 2. ከውጭ የሚመጡ ሰዎች የህዝብ ማጓጓዣዎች መውሰድ አይችሉም፡ መውሰድ ያለባቸው በግል ማጓጓዣ ብቻ ሲሆን፡ በመዳረሻ መጥቶ የሚወስዳቸው ( በ ኤርፖርት፣ ፖርት፣ ባቡር ጣብያ፥ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት፡ መኪና በመከራየት፡ በታክሲ ወይም የሚከራይ መኪና ከነ ሹፈሩ) ብቻ መሆን ኣለበት።   
 3. በኣሁኑ ሰዓት ማነኛውን ወደ ጣልያን የሚገባ ሰው ኳራንቴና ማድረግ ኣለበት። በግል መኪናው የሚገባም ጭምር። በስራ ወደ ጣልያን የሚገባ ኳራንቴናው ለማድረግ 72 ሰዓታት መቆየት ይችላል፡ በጣም ኣስፈላጊ በሆነ ምክንያት ብቻ (ለተጨማሪ 14 ሰዓታትም ማራዘም ይችላል)። 
 4. ሁሉም ከውጭ የሚገቡ ሰዎች፡ በግል መኪናቸውም ቢሆን፡ እንደገቡ ኃላፊነት ያለውን የአካባቢውን የጤና ባለሥልጣን ማሳወቅ አለባቸው ፡፡ 
 5. የሚወሸብበት፡ በቤቱ ብቻ ሳይሆን ባለጉዳዩ በሚመርጠው ቦታ መሆን ይቻላል።
 6. ኣንድ ሰው ወደ ጣልያን እንደገባ የኳራንቴና ውሸባ ግዜ የምያሳልፍበትቦታ ከሌለው (የሚቀበለው ሰው ከሌለ፣ በሆቴል ክፍል ካጣ ወዘተ ... ) የውሸባ ግዜው የሚያሳልፍበት፡ በባለጉዳዩ ወጪ፡ የሲቪል ጥበቃ በሚመድብለት ቦታ ይሆናል።
 7. ድንበር ተሻጋሪ ኣጓጓዦች፣ የሕክምና ሰራተኞች፣ የሰውና የጭነት ኣመላላሾች ይህን ህግ ኣይመለከታቸውም።

 

የጤና ሚኒስትሩ ትዕዛዝ ከመሠረተ ልማትና ትራንስፖርት ሚኒስትሩ ጋር በመመካከር 

 • በውጭ ኣገር የሚኖር የጣልያን ዜጋ ነኝ፡ ወይም ነዋሪነቴ በጣልያን የሆነ የውጭ ዜጋ ነኝ፡ ወደ ጣልያን መግባት እችላለሁ?

አዎ ፣ መመለስ በጣም አጣዳፊ ከሆነ። ስለዚህ ፣ ለምሳሌ ፣ ጊዜያዊ በሆነ ሁኔታ ወደ ውጭ አገር የሄዱ የጣልያን ዜጎች ወይም የውጭ ዜጎች (ለቱሪዝም ፣ ለንግድ ወይም ለሌላ) ተመልሰው ለመግባት ይፈቀዳል። እንደዚሁም፡ የሚሰሩበት ወይም የሚማሩበት ውጭ ሀገር ለመልቀቅ የተገደዱት የጣሊያን ዜጎችም ወደ ጣሊያን እንዲመለሱ ተፈቅዶላቸዋል (ለምሳሌ፣ ከስራቸው የተሰናበቱ፣ ቤታቸውን ያጡ፣ ትምህርታቸው ሙሉ በሙሉ ያቋረጡ)፡፡

 • እኔ የውጭ አገር ሰው ነኝ እና በአሁኑ ጊዜ ጣሊያን ውስጥ ነኝ፣ ወደ አገሬ መመለስ እችላለሁ?

አዎን ፣ የመመለሱ ጉዳይ ኣጣዳፊ ከሆነ፡ ልክ እንደ ጣልያኖች ከውጭ የሚመለሱበት ሁኔታ (ብዙ ግዜ የሚጠየቁና መልሰቹን እይ)። ግዝያዊ የስራ ማቆምና በቀጣይ የስራ መቆራረጥ ለመንቀሳቀስ ምክን ያት ሊሆኑ ኣይችሉም። ድንበሩን ለመድረስ አስፈላጊ ለሆኑት ምክንያቶች በራስየሚሞው ማረጋገጫ በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ድርገጽ ላይ የታተመው ቅፅ መጠቀም ይቻላል ፡፡

የቫይረሱ ስርጭትን በሚመለከት: የሚጓዙበት ሀገር የሚከተለውን እርምጃዎችና ሕጎች፡ ከመነሳትዎ በፊት በደንብ ማወቅ ይመከራል ፡፡ በተጨማሪ በጣልያን ያለውን የኣገሩ ኤምባሲ መጠየቅን ይመከራል።

 • ከውጭ እየተመለስኩ ነው ፡፡ ከአውሮፕላን ማረፊያ ፣ ከባቡር ጣቢያ ወይም ከመድረሻ ወደብ አንድ ሰው እንዲቀበለኝ መጠየቅ እችላለሁ?

አዎን ፣ ነገር ግን የሚፈቀደው፡ ለኣንድ በመኖርያ ቤት ኣብሮ ለሚኖረው ሰው ብቻ፡ በተቻለ መጠን ለቫይረሱ ስርጭት መከላከያ ቁሳቁሶች በመጠቀም። ከውጭ የሚመለሰው ሰው የሚመለስበት ኣጣዳፊ ምክንያት በመግለጽ፡ በኣገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በተዘጋጀው ቅጽ፤ የጉዞውን ዝርዝር ማለት ከየት ተነስቶ የት እንደሚያርፍና የሚያርፍበትን ኣድራሻ በቅጹ በደንብ ማስፈር ኣለበት።

ይህ እንዳለ ሆኖ፡ ጣልያን እንደገባ፡ የጤንነት ክትትል ለሚያደርገው የጤና ባለስልጣን ማሳወቅና ገለልተኛ ሆኖ የመቆየት ግዴታ ያለበት ሲሆን፡ በማንኛውም ግዜ የኮቪድ 19 የበሽታ ምልክት ከታየው በፍጥነት ለጤና ባለስልጣኑ የማሳወቅ ግዴታ ኣለበት።
የማፈናጠጥ ሕጎች

የጉዞና የመንቀሳቀስ ህጎች

 1. በጣልያን መንቀሳቀስ እችላለሁ?
  ብቁ ምክንያት ከሌለ ከቤት መውጣት ኣይፈቀድም። ጉዞ ወይንም የመንቀሳቀስን መገደብን በተመለከተ ከ10 ማርች ጀምሮ እስከ 3 ኣፕሪል በሁሉም የጣልያን ክልሎች ኣንድ ዓይነት ናቸው። በሁሉም ቦታዎች የፖሊሶች ቁጥጥር ይኖራል። በኳራንቴና ክትትል ለሚገኝና በቫይረሱ ፖዚቲቭ ለሆነ ከቤት መውጣት በትጥብቅ የተከለከለ ነው። በመተንፈሻ ኣካላት ኢንፌክሽን ካለ ወይም የሰውነት ትኩሳት ከ37.5 በላይ ከሆነ ከቤት መውጣት በጥብቅ የተከለከለ ነው። ቀጥሎም ሓኪሙን ማነጋገርና ከሌሎች ሰዎች መገናኘት ማቆም ነው።
 2. ከቤት ለመውጣት የሚያስችሉ ብቁ ምክንያቶች ምንድናቸው?
  በጤና ምክንያት ወይም በፍላጎት ምክንያት ወደ ሥራ ለመሄድ ቤቱን ለቀው መውጣት ይችላሉ ፡፡ እነዚህን ፍላጎቶች ለማረጋገጥ የራስ-መግለጫው መሞላት አለበት ፣ እሱም ለፖሊስ በሚቀርቡት ቅጾች ላይ በቀጥታ መቀመጥ ይችላል ፡፡ የማስታወቂያው ትክክለኛነት ለቀጣይ ማረጋገጫዎች ይገዛል ፡፡
 3. ከቤት ፣ ቤት ወይም መኖሪያ ርቆ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ወደ ቤት መመለስ ይችላል?
  አዎ ፣ ከዚያ ለስራ ፍላጎቶች ፣ ለችግር ሁኔታዎች እና ለጤንነት ምክንያቶች ብቻ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ተገንዝበዋል ፡፡
 4. በአንዱ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ የምኖር እና በሌላ ውስጥ የምሠራ ከሆነ ወደ ኋላ እና ወደ ፊት መሄድ እችላለሁን?
  አዎ ፣ ለንግድ ፍላጎቶች ተገቢነት ያለው ለውጥ ከሆነ ፡፡
 5. በሕዝብ ማመላለሻ ኣገልግሎት ተጠቅሜ መመላለስ እችላለሁ?
  የተከለከለ የትራንስፖርት ወይም የማመላለሻ ኣገልግሎት የለም። የሕዝብ ይሁን የግል ማመላለሻዎች እንደወትሮው ኣገልግሎት ይሰጣሉ።
 6. ኣስፈላጊ የምግብ ኣቅርቦት ለሟሟላት መውጣት ይቻላል?
  አዎ ፣ እና እነሱን መያዝ ምንም አያስፈልግም ምክንያቱም መደብሮች ሁልጊዜ የሚቀርቡ ናቸው ፡፡ የሸቀጣሸቀጦች መሸጋገሪያ ምንም ገደብ የለም ፤ ስለሆነም ሁሉም ሸቀጦች መሠረታዊ ፍላጎቶች ብቻ ሳይሆኑ በሀገራዊው ክልል ማሰራጨት ይችላሉ ፡፡
 7. ከምግብ ሸቀጦች የተለየ ሌላ እቃ ለመግዛት መውጣት ይቻላል?
  አዎ ፣ ግን በጥብቅ አስፈላጊነት ምክንያት ብቻ ፣ ስለሆነም ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ የማይችሉ ከዋና ፍላጎቶች ጋር የተዛመዱ እቃዎችን መግዣ ብቻ።
 8. ቤተሰቦቼ ወዳሉበት ቤት በመሄድ ከነሱ መብላት እችላለሁ?
  ኣትችልም። ኣስፈላጊ ስላልሆነ በመንቀሳቀሻ ፈቃዱ ኣልተካተተም።
 9. ኣቅም የሌላቸው ሽማግሌ ወላጆቼ ለመርዳት መሄድ እችላለሁ?
  አዎን ነገር ግን አዛውንቶች በጣም ተጋላጭ ሰዎች መሆናቸውን እና ስለዚህ በተቻለ መጠን ከእውቂያዎቻቸው ለመጠበቅ ሞክሩ ፡፡
 10. ከቤት ውጭ የሞተር እንቅስቃሴ ይፈቀዳል?
  በክፍት ቦታ ስፖርት መስራት የተፈቀደ ሲሆን፡ ስፖርተኞቹ ኣንድ ሜትር ተራርቀው መስራት ኣስፈላጊ ነው። ለማንኛውም ኣለመሰባሰብ ይመረጣል።
 11. ከውሻየ ጋር መውጣት እችላለሁ?
  አዎ ፣ ለዕለታዊ ፍላጎቶቹ ዕለታዊ አያያዝ እና ለእንስሳት ምርመራዎች ፡፡
 12. ህጉን የማያከብሩ ሰዎች ምን ይሆናሉ?
  በአርቲክል 650 የቅጣት ህግ ኮድ መሰረት፡ የሰዎስት ወር እስራት ወይም 206 ኤውሮ ይቀጣል። ለየት ያለ ኣላስፈላጊ ድርጊት ለሚፈጽሙ ግን ጠንከር ያለ ቅጣት ይቀጣሉ።

https://youtu.be/Y3jDeCG1G5shttps://youtu.be/q8GvFaNUR0ghttps://youtu.be/VdrRojUtjG4https://youtu.be/YDYm2g-gpKohttps://youtu.be/pXVenWV60AEhttps://youtu.be/K2sZcAGIYnkhttps://youtu.be/eGO6Wum1MzIhttps://youtu.be/fHp8SL-9g2Qhttps://youtu.be/FKTpeKDvnUwhttps://youtu.be/I2Rel57m1_4https://youtu.be/aDgCOCHBCk8https://youtu.be/50WzNN5gm5Ahttps://youtu.be/sMuszdu0l1Qhttps://youtu.be/jOszPIw_ctYhttps://youtu.be/PdeCcqXrd_Ihttps://youtu.be/Q-C6UrbrsPAhttps://youtu.be/exp5SXx-va8https://youtu.be/ba_OFCxeZoghttps://youtu.be/Y3jDeCG1G5shttps://youtu.be/q8GvFaNUR0ghttps://youtu.be/VdrRojUtjG4https://youtu.be/eGO6Wum1MzIhttps://youtu.be/K2sZcAGIYnkhttps://youtu.be/Te2FHINPT7ghttps://youtu.be/PdeCcqXrd_Ihttps://youtu.be/Q-C6UrbrsPAhttps://youtu.be/exp5SXx-va8https://youtu.be/ba_OFCxeZoghttps://youtu.be/j5loEOVqoCUhttps://youtu.be/YDYm2g-gpKo

ለ CORONAVIRUS ፊልሞች ራስን መቻል ማረጋገጫ

ቤትዎን ለቀው ለመውጣት በአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የተዘጋጀ ቅፅ መሙላት ያስፈልግዎታል ፡፡ ቅጹ ፣ መታተም እና መሙላት ያለበት ፣ በብሔራዊ ግዛቱ ሁሉ ልክ ነው።

[አዲሱን ቅፅ 03/26/2020 ለማውረድ እዚህ ጠቅ ያድርጉ]

እንዴት እንደሚሞሉት እነሆ-

ሰነዶች

የቪዲዮ

ፖድካስት

አማርኛ
Italiano English (UK) Français العربية বাংলা 简体中文 Español ਪੰਜਾਬੀ Русский Af Soomaali Shqip ትግርኛ اردو Wolof አማርኛ